Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

43 የጌ​ታዬ እናት ወደ እኔ ትመጪ ዘንድ እኔ ምን​ድን ነኝ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

43 ለመሆኑ የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እኔ ማን ነኝ?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ መምጣትዋ እንዴት ያለ ነገር ነው?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

43 የጌታዬ እናት ልትጐበኘኝ መምጣትዋ ለእኔ እንዴት ያለ ታላቅ ክብር ነው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

43 የጌታዬ እናት ወደ እኔ ትመጣ ዘንድ እንዴት ይሆንልኛል?

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:43
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ቶማ​ስም፥ “ጌታዬ አም​ላ​ኬም” ብሎ መለሰ።


በክ​ር​ክ​ርና ከንቱ ውዳ​ሴን በመ​ው​ደድ አት​ሥሩ፤ ትሕ​ት​ናን በያዘ ልቡና ከራ​ሳ​ችሁ ይልቅ ባል​ን​ጀ​ራ​ች​ሁን አክ​ብሩ እንጂ አት​ታ​በዩ።


እነሆ፥ ዛሬ በዳ​ዊት ከተማ መድ​ኅን ተወ​ል​ዶ​ላ​ች​ኋል፤ ይኸ​ውም ቡሩክ ጌታ ክር​ስ​ቶስ ነው።


አቤቱ፥ በቅ​ኖች ሸንጎ በጉ​ባ​ኤም በፍ​ጹም ልቤ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ተነ​ሥ​ታም በግ​ን​ባ​ርዋ በም​ድር ወድቃ ሰገ​ደ​ችና፥ “እነሆ፥ እኔ ገረ​ድህ የጌ​ታ​ዬን ሎሌ​ዎች እግር አጥብ ዘንድ አገ​ል​ጋይ ነኝ” አለች።


ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግ​ለው ዘንድ፥ ሁሉን የተ​ው​ሁ​ለት፥ እንደ ጕድ​ፍም ያደ​ረ​ግ​ሁ​ለት የጌ​ታ​ዬን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ኀይ​ልና ገና​ና​ነት ስለ​ማ​ውቅ ሁሉን እንደ ኢም​ንት ቈጠ​ር​ሁት።


እና​ንተ ‘መም​ህ​ራ​ችን፥ ጌታ​ች​ንም’ ትሉ​ኛ​ላ​ችሁ፤ መል​ካም ትላ​ላ​ችሁ፤ እኔ እን​ዲሁ ነኝና።


እኔም ወደ አንተ ልመጣ አይ​ገ​ባ​ኝም፤ ነገር ግን በቃ​ልህ እዘዝ፤ ብላ​ቴ​ና​ዬም ይድ​ናል።


ዮሐንስ ግን “እኔ በአንተ ልጠመቅ ያስፈልገኛል፤ አንተም ወደ እኔ ትመጣለህን?” ብሎ ይከለክለው ነበር።


በግምባርዋም ተደፍታ በምድር ላይ ሰገደችለት፦ እኔንስ ለመቀበል በምን ነገር በፊትህ ሞገስ አገኘሁ? እኔ እንግዳ አይደለሁምን? አለችው።


ገናም ለሕዝቡ ሲናገር፥ እነሆ፥ እናቱና ወንድሞቹ ሊነጋገሩት ፈልገው በውጭ ቆመው ነበር።


በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው።


እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች