Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:41 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

41 ኤል​ሳ​ቤ​ጥም የማ​ር​ያ​ምን ሰላ​ምታ በሰ​ማች ጊዜ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀ​ንዋ ዘለለ፤ በኤ​ል​ሣ​ቤ​ጥም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​ባት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ፣ ፅንሱ በማሕፀኗ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞላች፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ ኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ተሞልታ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

41 ኤልሳቤጥ የማርያምን የሰላምታ ቃል በሰማች ጊዜ በማሕፀንዋ የነበረው ሕፃን ዘለለ። ኤልሳቤጥም በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

41 ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ ፅንሱ በማኅፀንዋ ውስጥ ዘለለ፤ በኤልሳቤጥም መንፈስ ቅዱስ ሞላባት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:41
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ልጆ​ች​ዋም በሆ​ድዋ ውስጥ ይን​ቀ​ሳ​ቀሱ ነበር ፤ እር​ስ​ዋም፥ “እን​ዲህ እሆን ዘንድ ካለኝ ይህ ለእኔ ምኔ ነው?” አለች። ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ትለ​ምን ዘንድ ሄደች።


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ታላቅ ይሆ​ና​ልና የወ​ይን ጠጅና የሚ​ያ​ሰ​ክ​ርም መጠጥ ሁሉ አይ​ጠ​ጣም፤ ከእ​ናቱ ማሕ​ፀን ጀም​ሮም መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​በ​ታል።


ወደ ዘካ​ር​ያስ ቤትም ገብታ ለኤ​ል​ሣ​ቤጥ ሰላ​ምታ ሰጠ​ቻት።


በታ​ላቅ ቃልም ጮሃ እን​ዲህ አለች፥ “ከሴ​ቶች ተለ​ይ​ተሽ አንቺ የተ​ባ​ረ​ክሽ ነሽ፤ የማ​ኅ​ፀ​ን​ሽም ፍሬ ቡሩክ ነው።


እነሆ፥ ሰላ​ምታ ስት​ሰ​ጭኝ ቃል​ሽን በሰ​ማሁ ጊዜ፥ ፅንሱ በማ​ኅ​ፀኔ በደ​ስታ ዘሎ​አ​ልና።


በአ​ባቱ በዘ​ካ​ር​ያ​ስም መን​ፈስ ቅዱስ መላ​በት፤ እን​ዲ​ህም ብሎ ትን​ቢት ተና​ገረ፦


ጌታ​ችን ኢየ​ሱ​ስም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመ​ልቶ ከዮ​ር​ዳ​ኖስ ተመ​ለሰ፤ መን​ፈ​ስም ወደ ምድረ በዳ ወሰ​ደው።


ሁሉም መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተሞሉ፤ ይና​ገሩ ዘንድ መን​ፈስ ቅዱስ እንደ አደ​ላ​ቸው መጠ​ንም እየ​ራ​ሳ​ቸው በሀ​ገሩ ሁሉ ቋንቋ ይና​ገሩ ጀመሩ።


ያን​ጊ​ዜም በጴ​ጥ​ሮስ መን​ፈስ ቅዱስ ሞላ​በ​ትና እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እና​ንተ የሕ​ዝብ አለ​ቆ​ችና ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሆይ፥ ስሙ፤


ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ ከእ​ና​ንተ ወገን በመ​ል​ካም የተ​መ​ሰ​ከ​ረ​ላ​ቸ​ውን መን​ፈስ ቅዱ​ስና ጥበብ የሞ​ላ​ባ​ቸ​ውን ሰባት ሰዎ​ችን ምረጡ፤ ለዚህ ሥራም እን​ሾ​ማ​ቸ​ዋ​ለን።


በእ​ስ​ጢ​ፋ​ኖ​ስም ላይ መን​ፈስ ቅዱስ መላ፤ ወደ ሰማ​ይም ተመ​ለ​ከተ፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ክብር፥ ኢየ​ሱ​ስም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቀኝ ቆሞ አየ።


ያን​ጊ​ዜም ሐና​ንያ ሄደ፤ ወደ ቤትም ገባ፤ እጁ​ንም ጫነ​በ​ትና፥ “ወን​ድሜ ሳውል፥ በመ​ን​ገድ ስት​መጣ የታ​የህ ጌታ​ችን ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶስ ታይና መን​ፈስ ቅዱስ ይመ​ላ​ብህ ዘንድ ወደ አንተ ልኮ​ኛል” አለው።


መዳ​ራት ነውና ወይን በመ​ጠ​ጣት አት​ስ​ከሩ፤ መን​ፈስ ቅዱ​ስን ተመሉ እንጂ።


በጌታ ቀን በመንፈስ ነበርሁ፤ በኋላዬም የመለከትን ድምፅ የሚመስል ታላቅ ድምፅ ሰማሁ፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች