Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:22 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ወደ እነ​ርሱ ወደ ውጭ በወጣ ጊዜም እነ​ር​ሱን ማነ​ጋ​ገር ተሳ​ነው፤ በቤተ መቅ​ደ​ስም የተ​ገ​ለ​ጠ​ለት እን​ዳለ ዐወቁ፤ እን​ዲ​ሁም ዲዳ ሆኖ በእጁ እያ​መ​ለ​ከ​ታ​ቸው ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከወጣ በኋላም ሊያናግራቸው አልቻለም፤ በምልክት ከመጥቀስ በቀር መናገር ባለመቻሉ በቤተ መቅደስ ውስጥ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 በወጣም ጊዜ ሊያናግራቸው አልቻለም፤ በቤተ መቅደስም ውስጥ ራእይ እንዳየ ተገነዘቡ፤ እርሱም በምልክት ያናግራቸው ነበር፤ ዲዳም ሆኖ ቆየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ዘካርያስ ከቤተ መቅደስ በወጣ ጊዜ ከሰዎቹ ጋር መነጋገር አልቻለም፤ ስለዚህ እነርሱ በቤተ መቅደሱ ውስጥ ራእይ የታየው መሆኑን ዐወቁ፤ እርሱ በእጁ እየጠቀሰ ያስረዳቸው ነበር። በዚህም ሁኔታ ዱዳ ሆኖ ቈየ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 በወጣም ጊዜ ሊነግራቸው አልቻለም፥ በቤተ መቅደስም ራእይ እንዳየ አስተዋሉ፤ እርሱም ይጠቅሳቸው ነበር፤ ድዳም ሆኖ ኖረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:22
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እኔም ምላ​ስ​ህን ከት​ና​ጋህ ጋር አጣ​ብ​ቃ​ታ​ለሁ፤ አን​ተም ዲዳ ትሆ​ና​ለህ፤ እነ​ር​ሱም ዐመ​ፀኛ ቤት ናቸ​ውና የሚ​ዘ​ልፍ ሰው አት​ሆ​ን​ባ​ቸ​ውም።


ሕዝቡ ግን ዘካ​ር​ያ​ስን ይጠ​ብ​ቁት ነበር፤ በቤተ መቅ​ደስ ውስጥ ዘግ​ይቶ ነበ​ርና እጅግ ተደ​ነቁ።


ከዚ​ህም በኋላ የማ​ገ​ል​ገሉ ወራት በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ።


አባ​ቱ​ንም ጠቅ​ሰው፥ “ማን ሊሉት ትወ​ዳ​ለህ?” አሉት።


ስም​ዖን ጴጥ​ሮ​ስም እር​ሱን ጠቀ​ሰና፥ “ይህን ስለ ማን እንደ ተና​ገረ ጠይ​ቀህ ንገ​ረን” አለው።


እርሱ ግን ዝም እን​ዲሉ በእጁ አመ​ለ​ከ​ታ​ቸው፤ ከወ​ኅኒ ቤትም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ አወ​ጣው ነገ​ራ​ቸው፤ “ይህ​ንም ለያ​ዕ​ቆ​ብና ለወ​ን​ድ​ሞች ሁሉ ንገሩ” አላ​ቸው፤ ከዚ​ያም ወጥቶ ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ።


በዚያ የነ​በሩ አይ​ሁ​ድም እስ​ክ​ን​ድ​ሮስ የሚ​ባል አይ​ሁ​ዳዊ ሰውን ከመ​ካ​ከ​ላ​ቸው አስ​ነሡ፤ እር​ሱም ተነ​ሥቶ በእጁ ምል​ክት ሰጠና ለሕ​ዝቡ ሊከ​ራ​ከ​ር​ላ​ቸው ወደደ።


በፈ​ቀ​ደ​ለ​ትም ጊዜ ጳው​ሎስ በደ​ረ​ጃው ላይ ቆሞ እጁን ወደ ሕዝቡ ዘረጋ፤ እጅ​ግም ጸጥታ በሆነ ጊዜ ጳው​ሎስ በዕ​ብ​ራ​ይ​ስጥ ቋንቋ ተና​ገረ፤ እን​ዲ​ህም አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች