Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 ከእኛ አስ​ቀ​ድሞ በዐ​ይን ያዩ​ትና የቃሉ አገ​ል​ጋ​ዮች የነ​በሩ እንደ አስ​ተ​ላ​ለ​ፉ​ልን፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 ይህም ታሪክ ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ያስተላለፉልን ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት ለእኛ ባስተላለፉልን መሠረት፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 ይህን መልእክት ለእኛ ያስተላለፉልን ከመጀመሪያው አንሥቶ የዐይን ምስክሮችና የቃሉ አገልጋዮች የነበሩት ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:2
25 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እና​ን​ተም ትመ​ሰ​ክ​ራ​ላ​ችሁ፤ ከጥ​ንት ጀምሮ ከእኔ ጋር ኑራ​ች​ኋ​ልና።


ነገር ግን ተነ​ሣና በእ​ግ​ርህ ቁም፤ እኔን ባየ​ህ​በ​ትና ወደ​ፊ​ትም በም​ታ​ይ​በት ነገር አገ​ል​ጋ​ይና ምስ​ክር አድ​ርጌ ልሾ​ምህ ስለ​ዚህ ተገ​ል​ጬ​ል​ሃ​ለ​ሁና።


የእርሱን ግርማ አይተን እንጂ በብልሃት የተፈጠረውን ተረት ሳንከተል የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ኀይልና መምጣት አስታወቅናችሁ።


እኛስ እን​ዲህ ያለ​ውን ታላቅ መዳን ቸል ብን​ለው እን​ዴት እና​መ​ል​ጣ​ለን? ይህ በጌታ በመ​ጀ​መ​ሪያ የተ​ነ​ገረ ነበ​ረና የሰ​ሙ​ትም ለእኛ አጸ​ኑት።


የእግዚአብሔር ልጅ የኢየሱስ ክርስቶስ ወንጌል መጀመሪያ።


ሕማ​ማ​ትን ከተ​ቀ​በለ በኋላ ብዙ ተአ​ም​ራት በማ​ሳ​የት አርባ ቀን ሙሉ እየ​ተ​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው፥ ስለ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መን​ግ​ሥ​ትም እየ​ነ​ገ​ራ​ቸ​ውና እያ​ስ​ተ​ማ​ራ​ቸው ሕያው ሆኖ ራሱ​ን​ገ​ለ​ጠ​ላ​ቸው።


እንግዲህ እኔ ከእነርሱ ጋር ሽማግሌ የክርስቶስም መከራ ምስክር ደግሞም ሊገለጥ ካለው ክብር ተካፋይ የሆንሁ፥ በመካከላቸው ያሉትን ሽማግሌዎች እመክራቸዋለሁ፤


እኛስ ያየ​ነ​ው​ንና የሰ​ማ​ነ​ውን ከመ​ና​ገር ዝም እንል ዘንድ አን​ች​ልም።”


እና​ን​ተም ለዚህ ነገር ምስ​ክ​ሮች ናችሁ።


እኛ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋ​ዮ​ችና የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የም​ሥ​ጢሩ መጋ​ቢ​ዎች እንደ ሆን ሰው ስለ እኛ እን​ዲህ ያስብ።


ነገር ግን መን​ፈስ ቅዱስ በእ​ና​ንተ ላይ በወ​ረደ ጊዜ ኀይ​ልን ትቀ​በ​ላ​ላ​ችሁ፤ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌ​ምና በይ​ሁዳ ሁሉ፥ በሰ​ማ​ር​ያና እስከ ምድር ዳርቻ ድረ​ስም ምስ​ክ​ሮች ትሆ​ኑ​ኛ​ላ​ችሁ።”


ዘሪው ቃሉን ይዘራል። ቃልም በተዘራበት በመንገድ ዳር የሆኑት እነዚህ ናቸው፤


በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ኢየ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን አገ​ለ​ግል ዘንድ፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወን​ጌ​ልም እገዛ ዘንድ፥ በእኔ ትም​ህ​ርት አሕ​ዛብ በመ​ን​ፈስ ቅዱስ የተ​ወ​ደ​ደና የተ​መ​ረጠ መሥ​ዋ​ዕት ይሆኑ ዘንድ።


እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።


ነገር ግን ጊዜው ሲደ​ርስ እኔ እንደ ነገ​ር​ኋ​ችሁ ታስቡ ዘንድ ይህን ነገ​ር​ኋ​ችሁ። አስ​ቀ​ድሜ ግን ይህን አል​ነ​ገ​ር​ክ​ኋ​ች​ሁም ነበር፤ ከእ​ና​ንተ ጋር ነበ​ር​ሁና።


የተ​በ​ተ​ኑት ግን እየ​ተ​ዘ​ዋ​ወሩ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል ሰበኩ፥ አስ​ተ​ማ​ሩም።


ጴር​ጌን በተ​ባ​ለ​ችው ከተ​ማም ቃሉን ከተ​ና​ገሩ በኋላ ወደ ኢጣ​ሊያ ወረዱ።


ነገር ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃል በእ​ስያ እን​ዳ​ይ​ና​ገሩ መን​ፈስ ቅዱስ ስለ​ከ​ለ​ከ​ላ​ቸው ወደ ፍር​ግ​ያና ወደ ገላ​ትያ አው​ራጃ ሄዱ፤


በተ​ሰ​ሎ​ንቄ ካሉ​ትም እነ​ርሱ ይሻ​ላሉ፤ በፍ​ጹም ደስታ ቃላ​ቸ​ውን ተቀ​ብ​ለ​ዋ​ልና፤ ነገ​ሩም እንደ አስ​ተ​ማ​ሩ​አ​ቸው እንደ ሆነ ለመ​ረ​ዳት ዘወ​ትር መጻ​ሕ​ፍ​ትን ይመ​ረ​ምሩ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች