Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሉቃስ 1:1 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

1 በእኛ ዘንድ የተ​ፈ​ጸ​መ​ው​ንና የታ​መ​ነ​ውን የሥ​ራ​ውን ዜና በሥ​ር​ዐት ሊጽፉ የጀ​መሩ ብዙ​ዎች ናቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

1 በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ነገሮች ብዙዎች ታሪኩን የተቻላቸውን ያህል ጽፈውት ይገኛል፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

1 እጅግ የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ብዙዎች በእኛ መካከል ስለ ተፈጸሙት ክስተቶች በጽሑፍ ለማዘጋጀት እንደሞከሩት ሁሉ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

1 የተከበርክ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ በእኛ መካከል የተፈጸሙትን ነገሮች የሚገልጥ ታሪክ ከዚህ ቀደም ብዙዎች ጽፈዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

1-4 የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ፥ ከመጀመሪያው በዓይን ያዩትና የቃሉ አገልጋዮች የሆኑት እንዳስተላለፉልን፥ በኛ ዘንድ ስለ ተፈጸመው ነገር ብዙዎች ታሪክን በየተራው ለማዘጋጀት ስለ ሞከሩ፥ እኔ ደግሞ ስለ ተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ በጥንቃቄ ሁሉን ከመጀመሪያው ተከትዬ በየተራው ልጽፍልህ መልካም ሆኖ ታየኝ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሉቃስ 1:1
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግዚአብሔርንም የመምሰል ምሥጢር ያለ ጥርጥር ታላቅ ነው፤ በሥጋ የተገለጠ፥ በመንፈስ የጸደቀ፥ ለመላእክት የታየ፥ በአሕዛብ የተሰበከ፥ በዓለም የታመነ፥ በክብር ያረገ።


ነገር ግን ይህ የተ​ጻፈ ኢየ​ሱስ እርሱ ክር​ስ​ቶስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ እንደ ሆነ እና​ንተ ታምኑ ዘንድ፥ አም​ና​ች​ሁም በስሙ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕይ​ወ​ትን ታገኙ ዘንድ ነው።


ዳሩ ግን የስብከቱ ሥራ በእኔ እንዲፈጸም አሕዛብም ሁሉ እንዲሰሙት፥ ጌታ በእኔ አጠገብ ቆሞ አበረታኝ፤ ከአንበሳ አፍም ዳንሁ።


እነርሱም ወጥተው በየስፍራው ሁሉ ሰበኩ፤ ጌታም ከእነርሱ ጋር ይሠራ ነበር፤ በሚከተሉትም ምልክቶች ቃሉን ያጸና ነበር።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሰ​ጠ​ውን ተስፋ ሊያ​ደ​ር​ግ​ለት እን​ደ​ሚ​ችል በፍ​ጹም ልቡ አመነ።


ከቀን ቀን የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ዘወ​ት​ርም የሚ​ከ​ለ​ከል አለና፤ ነገር ግን ሁሉም ልቡ እንደ ወደደ ያድ​ርግ።


ይኸ​ውም ልቡ​ና​ቸው ደስ ይለው ዘንድ፥ ትም​ህ​ር​ታ​ቸ​ውም በማ​ወቅ፥ በፍ​ቅ​ርና ፍጹ​ም​ነት ባለው ባለ​ጸ​ግ​ነት፥ በጥ​በ​ብና በሃ​ይ​ማ​ኖት፥ ስለ ክር​ስ​ቶ​ስም የሆ​ነ​ውን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር በማ​ወቅ ይጸና ዘንድ ነው።


ከእ​ና​ንተ ወገን የሚ​ሆን ኤጳ​ፍ​ራ​ስም ሰላም ይላ​ች​ኋል፥ እርሱ የክ​ር​ስ​ቶስ አገ​ል​ጋይ ነው፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በሚ​ወ​ደው ነገር ሁሉ ምሉ​ኣ​ንና ፍጹ​ማን እን​ድ​ት​ሆኑ፥ ስለ እና​ንተ ዘወ​ትር ይጸ​ል​ያል፤ ይማ​ል​ዳ​ልም።


ወንጌላችን በኀይልና በመንፈስ ቅዱስ በብዙ መረዳትም እንጂ በቃል ብቻ ወደ እናንተ አልመጣምና፤ በእናንተ ዘንድ ስለ እናንተ እንዴት እንደ ነበርን ታውቃላችሁ።


ነገር ግን ሁላ​ች​ሁም በዚች ተስ​ፋ​ችሁ እን​ዲሁ ትጋ​ታ​ች​ሁን እስከ መጨ​ረ​ሻው ታሳዩ ዘንድ እን​ወ​ዳ​ለን።


እን​ግ​ዲህ ከክፉ ሕሊና ለመ​ን​ጻት ልባ​ች​ንን ተረ​ጭ​ተን፥ ሰው​ነ​ታ​ች​ን​ንም በጥሩ ውኃ ታጥ​በን በተ​ረ​ዳ​ን​በት እም​ነት በቅን ልብ እን​ቅ​ረብ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች