Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 9:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አረደ፤ የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በዙ​ሪ​ያው ረጨው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 ከዚህ በኋላ አሮን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ዐረደ፤ ልጆቹ ደሙን አቀበሉት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ረጨ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 የሚቃጠል መሥዋዕት ሆኖ የሚቀርበውንም እንስሳ ዐረደ፤ ልጆቹም ደሙን ወደ እርሱ አመጡለት፤ እርሱም ደሙን በመሠዊያው ጐን በአራቱም ማእዘን ረጨ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ እርሱም በመሠዊያው ላይ በዙሪያው ረጨው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 9:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሮ​ንም ሙሴን ተና​ገ​ረው እን​ዲ​ህም አለው፥ “እነሆ፥ ዛሬ የኀ​ጢ​አ​ታ​ቸ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸ​ውን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት በለዩ ጊዜ፥ ይህች አገ​ኘ​ችኝ፤ ዛሬም የኀ​ጢ​አ​ቱን መሥ​ዋ​ዕት እበላ ዘንድ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት መል​ካም አይ​ደ​ለም።”


ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት በየ​ብ​ልቱ፥ ራሱ​ንም አመ​ጡ​ለት፤ እር​ሱም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመ​ረው።


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ው​ንም መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ እንደ ሥር​ዐ​ቱም አደ​ረ​ገው።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።


ክር​ስ​ቶስ እንደ ወደ​ዳ​ችሁ፥ ራሱ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ የሚ​ሆን መሥ​ዋ​ዕ​ትና ቍር​ባን አድ​ርጎ እንደ ሰጠ​ላ​ችሁ በፍ​ቅር ተመ​ላ​ለሱ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች