Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 9:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ከኀ​ጢ​አቱ መሥ​ዋ​ዕት ስቡ​ንና ኵላ​ሊ​ቶ​ቹን፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት የኀጢአት መሥዋዕቱን ሥብ፣ ኵላሊቶቹንና የጕበቱን ሽፋን በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ከኃጢአቱ መሥዋዕት ስቡንና ኩላሊቶቹን፥ በጉበቱም ላይ ያለውን መረብ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከዚህም በኋላ ስቡን፥ ኲላሊቶቹን እንደ መረብ ሆኖ ጒበቱን ከሚሸፍነው ስብ ምርጥ የሆነውን ወስዶ እግዚአብሔር ሙሴን ባዘዘው መሠረት በመሠዊያው ላይ አቃጠለው፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ከኃጢአቱ መሥዋዕት ስቡንና ኵላሊቶቹን፥ የጕበቱንም መረብ በመሠዊያው ላይ አቃጠለ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 9:10
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።


ልጄ ሆይ፥ ልብህን ስጠኝ፥ ዐይኖችህም መንገዴን ይጠብቁ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


ለዘ​ለ​ዓ​ለም በአ​ር​ያም የሚ​ኖር ስሙም ቅዱሰ ቅዱ​ሳን የሆነ፥ በቅ​ዱ​ሳን አድሮ የሚ​ኖር፥ ለተ​ዋ​ረ​ዱት ትዕ​ግ​ሥ​ትን የሚ​ሰጥ፥ ልባ​ቸ​ውም ለተ​ቀ​ጠ​ቀጠ ሕይ​ወ​ትን የሚ​ሰጥ ልዑል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦


ይህ ሁሉ የእጄ ሥራ ነው፤ ይህም ሁሉ የእኔ ነው፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ “ወደ የዋ​ሁና ወደ ጸጥ​ተ​ኛው፥ ከቃ​ሌም የተ​ነሣ ወደ​ሚ​ን​ቀ​ጠ​ቀጥ ሰው ከአ​ል​ሆነ በቀር ወደ ማን እመ​ለ​ከ​ታ​ለሁ?


ሥጋ​ው​ንና ቍር​በ​ቱ​ንም ከሰ​ፈሩ ውጭ በእ​ሳት አቃ​ጠሉ።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ደሙን አቀ​ረ​ቡ​ለት፤ ጣቱ​ንም በደሙ ውስጥ ነክሮ የመ​ሠ​ዊ​ያ​ውን ቀን​ዶች ቀባ፤ ደሙ​ንም ከመ​ሠ​ዊ​ያው በታች አፈ​ሰ​ሰው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች