Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 8:13 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ሙሴ የአ​ሮ​ንን ልጆች አቀ​ረበ፤ የበ​ፍታ ቀሚ​ሶ​ች​ንም አለ​በ​ሳ​ቸው፤ በመ​ታ​ጠ​ቂ​ያም አስ​ታ​ጠ​ቃ​ቸው፤ አክ​ሊ​ልም ደፋ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እግዚአብሔርም ባዘዘው መሠረት ሙሴ፣ የአሮንን ልጆች ወደ ፊት አቅርቦ እጀ ጠባብ አለበሳቸው፤ መታጠቂያዎችን አስታጠቃቸው፤ ቆብም ደፋላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 ጌታም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመርገፍም በተጌጠ መታጠቂያ አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 ቀጥሎም ሙሴ እግዚአብሔር ባዘዘው መሠረት የአሮንን ወንዶች ልጆች ወደፊት አቅርቦ ቀሚስ አለበሳቸው፤ በወገባቸውም ዙሪያ መታጠቂያ አድርጎ በራሳቸውም ላይ ቆብ ደፋላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እግዚአብሔርም ሙሴን እንዳዘዘው ሙሴ የአሮንን ልጆች አቀረበ፥ ቀሚሶችንም አለበሳቸው፥ በመታጠቂያም አስታጠቃቸው፥ ቆብም ደፋባቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 8:13
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ለአ​ሮ​ንም የተ​ቀ​ደ​ሰ​ውን ልብስ ታለ​ብ​ሰ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ባ​ዋ​ለህ፤ ትቀ​ድ​ሰ​ው​ማ​ለህ፤ ካህ​ንም ይሆ​ነ​ኛል።


ሙሴም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ አደ​ረገ፤ እን​ዲ​ሁም አደ​ረገ።


በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እጅግ ደስ ይላ​ቸ​ዋል። ነፍ​ሴም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሐሤት ታደ​ር​ጋ​ለች። ሽል​ማ​ትን እንደ ለበሰ ሙሽራ፥ በጌጥ ሽል​ማ​ቷም እን​ዳ​ጌ​ጠች ሙሽራ፥ የማ​ዳ​ንን ልብስ አል​ብ​ሶ​ኛ​ልና፥ የደ​ስ​ታ​ንም መጐ​ና​ጸ​ፊያ ደር​ቦ​ል​ኛ​ልና።


እና​ንተ ግን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ካህ​ናት ትባ​ላ​ላ​ችሁ፤ የአ​ም​ላ​ካ​ች​ንም አገ​ል​ጋ​ዮች ተብ​ላ​ችሁ ትጠ​ራ​ላ​ችሁ፤ የአ​ሕ​ዛ​ብን ሀብት ትበ​ላ​ላ​ችሁ፤ በሀ​ብ​ታ​ቸ​ውም ትመ​ካ​ላ​ችሁ።


ካህ​ና​ቱም በገቡ ጊዜ ከመ​ቅ​ደሱ በው​ጭው አደ​ባ​ባይ አይ​ወ​ጡም፤ የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉ​በ​ትን ልብ​ሳ​ቸ​ውን ግን ቅዱስ ነውና በዚያ ያኖ​ሩ​ታል፤ ሌላም ልብስ ለብ​ሰው ወደ ሕዝብ ይወ​ጣሉ።”


እነ​ር​ሱም ገብ​ተው አነ​ሡ​አ​ቸው፤ ሙሴም እን​ዳለ በል​ብ​ሳ​ቸው ከሰ​ፈር ወደ ውጭ ወሰ​ዱ​አ​ቸው።


የሆድ ዕቃ​ው​ንና እግ​ሮ​ቹ​ንም በውኃ አጠበ፤ ሙሴም አው​ራ​ውን በግ ሁሉ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ጨመረ፤ ይህ በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነበረ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የእ​ሳት ቍር​ባን ነበረ።


እናንተ ደግሞ እንደ ሕያዋን ድንጋዮች ሆናችሁ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ለእግዚአብሔር ደስ የሚያሰኝ መንፈሳዊ መሥዋዕትን ታቀርቡ ዘንድ ቅዱሳን ካህናት እንድትሆኑ መንፈሳዊ ቤት ለመሆን ተሠሩ።


እናንተ ግን ከጨለማ ወደሚደነቅ ብርሃኑ የጠራችሁን የእርሱን በጎነት እንድትናገሩ የተመረጠ ትውልድ፥ የንጉሥ ካህናት፥ ቅዱስ ሕዝብ፥ ለርስቱ የተለየ ወገን ናችሁ፤


መንግሥትም፥ ለአባቱም ለእግዚአብሔር ካህናት እንድንሆን ላደረገ፥ ለእርሱ ከዘላለም እስከ ዘላለም ድረስ ክብርና ኀይል ይሁን፤ አሜን።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች