Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 7:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ካህ​ኑም ስቡን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረው፤ ፍር​ም​ባ​ውም ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆቹ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ካህኑ ሥቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሰጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባው ግን ለአሮንና ለልጆቹ ይሆናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ካህኑ ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ፍርምባው ግን ለካህናቱ ይሰጥ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ካህኑም ስቡን በመሠዊያው ላይ ያቃጥላል፤ ፍርምባውም ለአሮንና ለልጆቹ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 7:31
13 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለአ​ሮ​ንም ክህ​ነት የታ​ረ​ደ​ውን የአ​ው​ራ​ውን በግ ፍር​ምባ ወስ​ደህ ለሚ​ለይ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ትለ​የ​ዋ​ለህ፤ እር​ሱም የአ​ንተ ወግ ይሆ​ናል።


ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ በጎ መዓዛ ያለው ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው።


ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።


የአ​ሮ​ንም ልጆች ከሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ጋር በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ሳቱ ላይ ባለው በዕ​ን​ጨቱ ላይ ያቀ​ር​ቡ​ታል፤ የእ​ሳት ቍር​ባን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ነው።


ካህ​ኑም ከእ​ነ​ዚያ በአ​ን​ዳ​ቸው ስለ ሠራው ኀጢ​አት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል። የተ​ረ​ፈ​ውም እንደ እህሉ ቍር​ባን ለካ​ህኑ ይሆ​ናል።”


ከእ​ር​ሱም የተ​ረ​ፈ​ውን አሮ​ንና ልጆቹ ይበ​ሉ​ታል፤ ቂጣ ሆኖ በተ​ቀ​ደ​ሰው ስፍራ ይበ​ላል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ ባለው አደ​ባ​ባይ ይበ​ሉ​ታል።


የሚ​ሠ​ዋው ካህን ይበ​ላ​ዋል፤ በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ዙሪያ በአ​ለው አደ​ባ​ባይ በተ​ቀ​ደሰ ስፍራ ይበ​ሉ​ታል።


ፍር​ም​ባ​ው​ንና የቀኝ ወር​ቹን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕ​ታ​ቸው ወስ​ጄ​አ​ለሁ፤ ለካ​ህኑ ለአ​ሮ​ንና ለል​ጆ​ቹም ለዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ዘንድ ሰጥ​ቼ​አ​ቸ​ዋ​ለሁ።”


ሙሴም ከቅ​ድ​ስ​ናው አውራ በግ ፍር​ም​ባ​ውን ወስዶ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በው ዘንድ ቈራ​ረጠ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴን እን​ዳ​ዘ​ዘው ይህ ለቅ​ድ​ስና ከታ​ረ​ደው አውራ በግ የሙሴ እድል ፈንታ ሆነ።


ይህም ለእ​ና​ንተ ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ለስ​ጦታ ያቀ​ረ​ቡ​ትን የመ​ጀ​መ​ሪያ ቍር​ባን ሁሉ ለአ​ንተ ከአ​ን​ተም ጋር ለወ​ን​ዶ​ችና ለሴ​ቶች ልጆ​ችህ የዘ​ለ​ዓ​ለም ሕግ እን​ዲ​ሆን ሰጥ​ቼ​ሃ​ለሁ፤ በቤ​ትህ ውስጥ ንጹሕ የሆነ ሁሉ ይብ​ላው።


ሥጋ​ውም ለአ​ንተ ይሆ​ናል፤ እን​ደ​ሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ፍር​ምባ እንደ ቀኙም ወርች ለአ​ንተ ይሆ​ናል።


የጣ​ዖ​ታቱ ካህ​ናት የጣ​ዖ​ታ​ቱን መባ እን​ደ​ሚ​በሉ አታ​ው​ቁ​ምን? መሠ​ዊ​ያ​ውን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግ​ሉም መሥ​ዋ​ዕ​ቱን እን​ደ​ሚ​ካ​ፈሉ አታ​ው​ቁ​ምን? ለቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሹሞች መተ​ዳ​ደ​ሪ​ያ​ቸው የቤተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መባ ነው።


በሬ ወይም በግ ለመ​ሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ያ​ቀ​ር​ቡት ሕዝብ የካ​ህ​ናቱ ወግ ይህ ይሆ​ናል፤ ወር​ቹ​ንና ሁለ​ቱን ጕን​ጮ​ቹን፥ ጨጓ​ራ​ው​ንም ለካ​ህኑ ይሰ​ጣሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች