ዘሌዋውያን 6:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)12 እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፤ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ ዕንጨት ያቃጥልበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም12 በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ዘወትር ይንደድ፤ ምን ጊዜም አይጥፋ። ካህኑ ጧት ጧት እሳቱ ላይ ማገዶ ይጨምር፤ በእሳቱ ላይ የሚቃጠለውን መሥዋዕት ያዘጋጅ፤ በዚህም ላይ የኅብረት መሥዋዕቱን ሥብ ያቃጥል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)12 እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይንደድበት፥ አይጥፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥለበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ እንዲሁም የአንድነትን መሥዋዕት ስብ በዚያ ላይ ያቃጥላል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም12 በመሠዊያው ላይ ያለው እሳት ሳይጠፋ ሌሊትና ቀን ዘወትር ሲነድ ይኑር፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ የማገዶ እንጨት ይጨምርበት፤ በእርሱ ላይ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት አመቻችቶ በማኖር የአንድነት መሥዋዕቱን ስብ ያቃጥለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)12 እሳቱም በመሠዊያው ላይ ዘወትር ይነድዳል፥ አይጠፋም፤ ካህኑም ማለዳ ማለዳ እንጨት ያቃጥለበታል፤ የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በዚያ ላይ ይረበርባል፤ በዚያም የደኅንነትን መሥዋዕት ስብ ያቃጥላል። ምዕራፉን ተመልከት |