Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 5:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 ነውር የሌ​ለ​በ​ትን በሰ​ቅል የተ​ገ​መ​ተ​ውን አውራ በግ ከመ​ን​ጋው ለበ​ደል መሥ​ዋ​ዕት ወደ ካህኑ ያመ​ጣ​ዋል፤ ካህ​ኑም ሳያ​ውቅ ስለ ሳተው ስሕ​ተት ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 እርሱም ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት የሚሆን እንከን የሌለበት አውራ በግ ወደ ካህኑ ያምጣ፤ ዋጋውም ተመጣጣኝ ይሁን። ካህኑም በዚህ ሁኔታ ሰውየው ሳያውቅ ስለ ፈጸመው ስሕተት ያስተሰርይለታል፤ ሰውየውም ይቅር ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው እንደ ግምጋሜህ መጠን ለበደል መሥዋዕት ወደ ካህኑ ያመጣል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሠራው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከመንጋው ምንም ነውር የሌለበት ተባዕት በግ ስለ በደሉ መሥዋዕት አድርጎ ወደ ካህን ያምጣ፤ ዋጋውም ተገምግሞ በይፋ በታወቀው ተመን ይወሰን፤ ካህኑም የእንስሳውን መሥዋዕት ስለዚያ ሰው ያቅርብ፤ በደል የሠራውም ሰው ኃጢአቱ ይቅር ይባልለታል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 ነውር የሌለበትን አውራ በግ ከመንጋው ለበደል መሥዋዕት እንደ ግምጋሜህ መጠን ወደ ካህኑ ያመጣዋል፤ ካህኑም ሳያውቅ ስለ ሳተው ስሕተት ያስተሰርይለታል፥ እርሱም ይቅር ይባላል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 5:18
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“መባ​ውም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከላ​ሞች መንጋ ቢሆን፥ ነውር የሌ​ለ​በ​ትን ተባ​ቱን ያቀ​ር​ባል፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት እን​ዲ​ኖ​ረው በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል።


ተቀ​ባ​ይ​ነት ይኖ​ረው ዘንድ ስለ እር​ሱም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለት ዘንድ እጁን በሚ​ቃ​ጠ​ለው መሥ​ዋ​ዕት ራስ ላይ ይጭ​ናል።


ካህ​ኑም አን​ዱን ጠቦት ወስዶ ስለ በደል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ያንም አንድ ማሰሮ ዘይት ስለ ልዩ ቍር​ባን በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ይለ​የ​ዋል።


እን​ዲ​ህም በወ​ይ​ፈኑ ያደ​ር​ጋል፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት በታ​ረ​ደው ወይ​ፈን እንደ አደ​ረገ እን​ዲሁ በዚህ ያደ​ር​ጋል፤ ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውን ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቸ​ውም ይሰ​ረ​ይ​ላ​ቸ​ዋል።


“ሰው ባለ​ማ​ወቅ ኀጢ​አት ቢሠራ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፦ አት​ሥሩ ካላ​ቸው ትእ​ዛ​ዛት አን​ዲ​ቱን ቢተ​ላ​ለፍ፥ ቢታ​ወ​ቀው፥ ኀጢ​አት ስለ​ሆ​ነ​ች​በ​ትም ንስሓ ቢገባ፥


እርሱ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ንስሓ ገብ​ቶ​አ​ልና።”


በማ​ኅ​በ​ሩም ፊት ያል​ታ​ወቀ ኀጢ​አት ቢኖር፥ ማኅ​በሩ ሁሉ ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ትና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ከመ​ን​ጋ​ዎች አንድ ንጹሕ ወይ​ፈን ያቀ​ር​ባሉ። የእ​ህሉ ቍር​ባ​ንና የመ​ጠጡ ቍር​ባ​ንም እንደ ሕጉ ነው፤ ለኀ​ጢ​አ​ትም መሥ​ዋ​ዕት አንድ አውራ ፍየል ያቀ​ር​ባሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች