Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 3:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 ካህ​ኑም በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ ያለው የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ነው። ስቡ ሁሉ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ካህኑም ይህን ሁሉ በእሳት የሚቀርብና ሽታውም ደስ የሚያሰኝ የመብል ቍርባን አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥል፤ ሥብ ሁሉ የእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ካህኑም መዓዛው ያማረ ሽታ እንዲሆን በእሳት የሚቀርብ ማዕድ አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል። ስቡ ሁሉ ለጌታ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ካህኑ ይህን ሁሉ መዓዛው እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ መሥዋዕት አድርጎ በመሠዊያው ላይ ያቃጥለው፤ ስብ ሁሉ ለእግዚአብሔር የተለየ ይሁን።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 ካህኑም በመሠዊያው ላይ ያቃጥለዋል፤ በእሳት ላይ ጣፋጭ ሽታ እንዲሆን የተደረገ መብል ነው። ስቡ ሁሉ ለእግዚአብሔር ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 3:16
19 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤ​ልም ደግሞ ከበ​ጎቹ መጀ​መ​ሪያ የተ​ወ​ለ​ደ​ው​ንና ከሰ​ቡት አቀ​ረበ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወደ አቤ​ልና ወደ መሥ​ዋ​ዕቱ ተመ​ለ​ከተ፤


የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከደ​ኅ​ን​ነቱ መሥ​ዋ​ዕት ስብና ለሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውም መሥ​ዋ​ዕት ከሚ​ቀ​ር​በው የመ​ጠጥ ቍር​ባን ጋር ብዙ ነበረ። እን​ዲ​ሁም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አገ​ል​ግ​ሎት ተዘ​ጋጀ።


ሰሎ​ሞ​ንም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ፊት የነ​በ​ረ​ውን የአ​ደ​ባ​ባ​ዩን ውስጥ ቀደሰ፤ ሰሎ​ሞ​ንም የሠ​ራው የናስ መሠ​ዊያ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የእ​ህ​ሉን ቍር​ባን፥ ስቡ​ንም መያዝ አል​ቻ​ለ​ምና የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕ​ትና የደ​ኅ​ን​ነ​ቱ​ንም መሥ​ዋ​ዕት፥ ስብ በዚያ አቀ​ረበ።


የሆድ ዕቃ​ው​ንም የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ ሁሉ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ያለ​ውን ስብ ወስ​ደህ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ታስ​ቀ​ም​ጣ​ለህ።


የበ​ጉ​ንም ስብ፥ የሆድ ዕቃ​ውን የሚ​ሸ​ፍ​ነ​ውን ስብ፥ በጉ​በ​ቱም ላይ ያለ​ውን መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ በላ​ያ​ቸ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ፥ የቀ​ኙ​ንም ወርች ትወ​ስ​ዳ​ለህ፤ የሚ​ቀ​ደ​ሱ​በት ነውና።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከግ​ር​ፋቱ ያነ​ጻው ዘንድ ፈቀደ፤ ስለ ኀጢ​አት መሥ​ዋ​ዕ​ትን ብታ​ቀ​ርቡ ሰው​ነ​ታ​ችሁ ረዥም ዕድሜ ያለ​ውን ዘር ታያ​ለች።


“ነገር ግን የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ከእኔ ዘንድ በሳቱ ጊዜ የመ​ቅ​ደ​ሴን ሥር​ዐት የጠ​በቁ የሳ​ዶቅ ልጆች ሌዋ​ው​ያን ካህ​ናት ያገ​ለ​ግ​ሉኝ ዘንድ ወደ እኔ ይቀ​ር​ባሉ፤ ስቡ​ንና ደሙ​ንም ወደ እኔ ያቀ​ርቡ ዘንድ በፊቴ ይቆ​ማሉ፥ ይላል ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


ካህ​ኑም በም​ስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ባለው በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ደሙን ይረ​ጨ​ዋል፤ ስቡ​ንም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን ያቃ​ጥ​ለ​ዋል።


ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


ስቡም ሁሉ ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ላይ እን​ደ​ሚ​ወ​ሰድ፥ ስብ​ዋን ሁሉ ይወ​ስ​ዳል፤ ካህ​ኑም ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በጎ መዓዛ እን​ዲ​ሆን በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል፤ ካህ​ኑም ስለ እርሱ ያስ​ተ​ሰ​ር​ያል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይሰ​ረ​ይ​ለ​ታል።


ስቡ​ንና ላቱን፥ በሆድ ዕቃ​ውም ላይ ያለ​ውን ስብ ሁሉ፥ የጉ​በ​ቱ​ንም መረብ፥ ሁለ​ቱ​ንም ኵላ​ሊ​ቶች፥ ስባ​ቸ​ው​ንም፥ ቀኝ ወር​ቹ​ንም ወሰደ፤


እሳ​ትም ከእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ዘንድ ወጣ፤ በመ​ሠ​ዊ​ያ​ውም ላይ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት፥ ስቡ​ንም በላ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አይ​ተው ተደ​ነቁ፤ በግ​ም​ባ​ራ​ቸ​ውም ወደቁ።


ኢየሱስም እንዲህ አለው “ ‘ጌታ አምላክህን በፍጹም ልብህ በፍጹም ነፍስህም በፍጹም አሳብህም ውደድ።’


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች