Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 22:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 በኀ​ጢ​አት ሳሉ ከተ​ቀ​ደ​ሰው መሥ​ዋ​ዕት ከበሉ ግን ኀጢ​አ​ትና በደል ይሆ​ን​ባ​ቸ​ዋል፤ የማ​ነ​ጻ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 ይህንኑ የተቀደሰ መሥዋዕት እንዲበሉና ቅጣት የሚያስከትል በደል እንዲፈጽሙ አያድርጉ፤ የምቀድሳቸው እኔ እግዚአብሔር ነኝ።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 ከዚህም የተነሣ የምቀድሳቸው እኔ ጌታ ነኝና የእነርሱን የተቀደሰ ነገር በሚበሉበት ጊዜ ኃጢአትንና በደልን እንዳይሸከሙ ነው።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 ይኸውም መብላት ለማይፈቀድለት ሰው ቢሰጡት በደል ሆኖ በዚያ ሰው ላይ ቅጣት ያስከትልበታል፤ ስጦታዎችን ሁሉ የምቀድስ እኔ እግዚአብሔር ነኝ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 22:16
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አቤቱ፥ ፍጻ​ሜ​ዬን አስ​ታ​ው​ቀኝ” አልሁ፥ የዘ​መኔ ቍጥ​ሮች ምን ያህል ናቸው? ዐውቅ ዘን​ድስ ለምን ወደ ኋላ እላ​ለሁ?


በአ​ሮ​ንም ግን​ባር ላይ ይሆ​ናል፤ አሮ​ንም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች በሚ​ያ​ቀ​ር​ቡ​ትና በሚ​ቀ​ድ​ሱት በቅ​ዱሱ ስጦ​ታ​ቸው ሁሉ ላይ የሠ​ሩ​ትን ኀጢ​አት ይሸ​ከም፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ተቀ​ባ​ይ​ነት ያለው እን​ዲ​ሆ​ን​ላ​ቸው ሁል​ጊዜ በግ​ን​ባሩ ላይ ይሁን።


“ቅዱሰ ቅዱ​ሳን ነውና፥ የሕ​ዝ​ቡ​ንም ኀጢ​አት እን​ድ​ት​ሸ​ከሙ፥ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት እን​ድ​ታ​ስ​ተ​ሰ​ር​ዩ​ላ​ቸው ይህን ትበሉ ዘንድ ለእ​ና​ንተ ሰጥ​ቶ​ታ​ልና ስለ ምን የኀ​ጢ​አ​ትን መሥ​ዋ​ዕት በቅ​ዱሱ ስፍራ አል​በ​ላ​ች​ሁም?


ሕጌ​ንና ትእ​ዛ​ዜን ጠብቁ፤ አድ​ር​ጉ​ትም፤ እኔ የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ካ​ችሁ ነኝና።


እኔም የም​ቀ​ድ​ሰው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና በሕ​ዝቡ መካ​ከል ዘሩን አያ​ጐ​ስ​ቍል።”


ነገር ግን ነው​ረኛ ነውና መቅ​ደ​ሶ​ችን እን​ዳ​ያ​ረ​ክስ ወደ መጋ​ረ​ጃው አይ​ግባ፤ ወደ መሠ​ዊ​ያ​ውም አይ​ቅ​ረብ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።”


የአ​ም​ላ​ክ​ህን መባ ያቀ​ር​ባ​ልና ስለ​ዚህ ትቀ​ድ​ሰ​ዋ​ለህ፤ እኔም የም​ቀ​ድ​ሳ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቅዱስ ነኝና እርሱ ቅዱስ ይሁ​ን​ልህ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ሙሴን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ረው፦


ቢያ​ረ​ክ​ሱ​አት እን​ዳ​ይ​ሞቱ፥ ስለ እር​ስ​ዋም ኀጢ​አ​ትን እን​ዳ​ይ​ሸ​ከሙ፥ ሕግን ይጠ​ብቁ፤ የም​ቀ​ድ​ሳ​ቸው እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝና።


በሦ​ስ​ተ​ኛው ቀን ከደ​ኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ሥጋ ቢበላ፥ አይ​ሠ​ም​ርም፤ ላቀ​ረ​በው ሰው የተ​ጠላ ይሆ​ን​በ​ታል እንጂ ቍር​ባን ሆኖ አይ​ቈ​ጠ​ር​ለ​ትም፤ ከእ​ር​ሱም የበላ ሰው ኀጢ​አ​ቱን ይሸ​ከ​ማል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ነገ​ረው፥ “አንተ ከአ​ን​ተም ጋር ልጆ​ች​ህና የአ​ባ​ቶ​ችህ ወገ​ኖች፥ የክ​ህ​ነ​ታ​ች​ሁን ኀጢ​አት ትሸ​ከ​ማ​ላ​ችሁ።


የመ​ጀ​መ​ሪ​ያ​ው​ንም ከእ​ርሱ ባነ​ሣ​ችሁ ጊዜ ስለ እርሱ ኀጢ​አት አይ​ሆ​ን​ባ​ች​ሁም፤ እን​ዳ​ት​ሞ​ቱም የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች የቀ​ደ​ሱ​ትን አታ​ር​ክሱ።”


እናንተ ደንቆሮዎችና ዕውሮች! ማናቸው ይበልጣል? ወርቁ ነውን? ወይስ ወርቁን የቀደሰው ቤተ መቅደስ?


ለኀጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኀጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፤ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች