Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 20:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

9 ማና​ቸ​ውም ሰው አባ​ቱን ወይም እና​ቱን ቢሰ​ድብ ፈጽሞ ይገ​ደል፤ አባ​ቱ​ንና እና​ቱን ሰድ​ቦ​አ​ልና በደ​ለኛ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

9 “ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሚረግም ማንኛውም ሰው ይገደል፤ አባቱን ወይም እናቱን ረግሟልና ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

9 ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፤ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፥ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

9 ማንኛውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ይገደል፤ አባቱንና ወይም እናቱን ስለ ሰደበ ሞት የተፈረደበት በራሱ በደል ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

9 ማናቸውም ሰው አባቱን ወይም እናቱን ቢሰድብ ፈጽሞ ይገደል፥ አባቱንና እናቱን ሰድቦአልና፤ ደሙ በራሱ ላይ ነው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 20:9
17 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ዳዊ​ትም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቀ​ባ​ውን እኔ ገድ​ያ​ለሁ ብሎ አፍህ በላ​ይህ መስ​ክ​ሮ​አ​ልና ደምህ በራ​ስህ ላይ ይሁን” አለው።


አባቴ ዳዊት ሳያ​ውቅ ከእ​ርሱ የሚ​ሻ​ሉ​ትን ሁለ​ቱን ጻድ​ቃን ሰዎች፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሠራ​ዊት አለቃ የኔ​ርን ልጅ አበ​ኔ​ርን፥ የይ​ሁ​ዳ​ንም ሠራ​ዊት አለቃ የኢ​ያ​ቴ​ርን ልጅ አሜ​ሳ​ይን በሰ​ይፍ ገድ​ሎ​አ​ልና እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዐ​መፅ ደሙን በራሱ ላይ መለሰ።


“ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አን​ዱን የሰ​ረቀ ወይም ግፍ የፈ​ጸ​መ​በት፥ ወይም አሳ​ልፎ ቢሰ​ጠው፥ ወይም በእ​ርሱ ዘንድ ቢገኝ፥ እርሱ ይገ​ደል።


አባቱንና እናቱን የሚያማ ብርሃኑ ይጠፋል፥ የዐይኖቹ ብሌንም ጨለማን ያያል።


በአ​ራጣ ቢያ​በ​ድር፥ አት​ር​ፎም ቢወ​ስድ፥ እን​ደ​ዚህ ያለ ሰው በሕ​ይ​ወት አይ​ኖ​ርም፤ ይህን ርኵ​ሰት ሁሉ አድ​ር​ጎ​አ​ልና ፈጽሞ ይሞ​ታል፤ ደሙም በላዩ ይሆ​ናል።


በአ​ንቺ ውስጥ አባ​ት​ንና እና​ትን አቃ​ለሉ፤ በመ​ካ​ከ​ልሽ በመ​ጻ​ተ​ኛው ላይ በደ​ልን አደ​ረጉ፤ በአ​ንቺ ውስጥ ድሀ አደ​ጉ​ንና መበ​ለ​ቲ​ቱን አስ​ጨ​ነቁ።


ማን​ኛ​ዪ​ቱም ሴት ወደ እን​ስሳ ብት​ቀ​ርብ፥ ከእ​ር​ሱም ጋር ብት​ገ​ናኝ፥ ሴቲ​ቱ​ንና እን​ስ​ሳ​ውን ግደሉ፤ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በደ​ለ​ኞች ናቸው።


“ወንድ ወይም ሴት መና​ፍ​ስ​ትን ቢጠሩ፥ ወይም ጠን​ቋ​ዮች ቢሆኑ ፈጽ​መው ይገ​ደሉ፤ በድ​ን​ጋ​ይም ይው​ገ​ሩ​አ​ቸው፤ በደ​ለ​ኞች ናቸ​ውና።”


እግዚአብሔር ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞ ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና፤


ሕዝቡም ሁሉ መልሰው “ደሙ በእኛና በልጆቻችን ላይ ይሁን፤” አሉ።


ሙሴ ‘አባትህንና እናትህን አክብር፤’ ደግሞም ‘አባቱን ወይም እናቱን የሰደበ ፈጽሞ ይሙት፤’ ብሎአልና።


“አባ​ቱን ወይም እና​ቱን የሚ​ያ​ቃ​ልል ርጉም ይሁን፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ አሜን ይላሉ።


ከቤ​ት​ሽም ደጅ ወደ ሜዳ የሚ​ወጣ ሁሉ ደሙ በራሱ ላይ ይሆ​ናል፤ እኛም ከዚህ ካማ​ል​ሽን መሐላ ንጹ​ሓን እን​ሆ​ና​ለን፤ ነገር ግን ከአ​ንቺ ጋር በቤ​ትሽ ውስጥ ያለ ቢሞት ደሙ በእኛ ላይ ነው።


ይህም የሆ​ነው፥ በሰ​ባው የይ​ሩ​በ​ኣል ልጆች ላይ የተ​ደ​ረ​ገው ዐመፅ እን​ዲ​መጣ፥ ደማ​ቸ​ውም በገ​ደ​ላ​ቸው በወ​ን​ድ​ማ​ቸው በአ​ቤ​ሜ​ሌክ ላይ፥ ወን​ድ​ሞ​ቹ​ንም እን​ዲ​ገ​ድል እጆ​ቹን ባጸ​ኑ​አ​ቸው በሰ​ቂማ ሰዎች ላይ እን​ዲ​ሆን ነው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች