ዘሌዋውያን 13:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ ምልክቱ በቆዳው ላይ ቢሰፋ ካህኑ፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ ለምጽ ነውና። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ካህኑም ይመርምረው፤ ችፍታው በቈዳው ላይ ተስፋፍቶ ከተገኘ፣ ካህኑ ሰውየው ርኩስ መሆኑን ያስታውቅ፤ ተላላፊ የቈዳ በሽታ ነው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ እከኩ በቆዳው ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ እርሱ የለምጽ ደዌ ነው። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 ካህኑም እንደገና ይመርምረው፤ ቊስሉም ተስፋፍቶ ከተገኘ የሥጋ ደዌ በሽታ ስለ ሆነ የረከሰ የሥጋ ደዌ በሽተኛ መሆኑን ያስታውቅ። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ካህኑም ያያል፤ እነሆም፥ እከኩ በቁርበቱ ላይ ቢሰፋ፥ ካህኑ፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ ለምጽ ነው። ምዕራፉን ተመልከት |