ዘሌዋውያን 13:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 እርሱ በሥጋው ቆዳ ላይ አሮጌ ለምጽ ነው፤ ካህኑም፦ ‘ርኩስ ነው’ ይለዋል፤ እርሱ ርኩስ ነውና ይለየዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም11 ሥር የሰደደ የቈዳ በሽታ ነውና ሰውየው ርኩስ መሆኑን ካህኑ ያስታውቅ፤ ርኩስ መሆኑ ግልጽ ስለ ሆነም ሰውየውን አያግልለው። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 እርሱ በሰውነቱ ቆዳ ላይ የቈየ የለምጽ ደዌ ነው፥ ካህኑም፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ እርሱ ርኩስ ነውና አይለየውም። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እርሱ በቈዳው ላይ የቈየ የሥጋ ደዌ ስለ ሆነ ካህኑ ሕመምተኛው የረከሰ መሆኑን ያስታውቅ፤ የረከሰ መሆኑ በግልጥ ስለ ታወቀ እንደዚህ ያለው ሰው በቤት ውስጥ ተዘግቶበት መቈየት አያስፈልገውም። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 እርሱ በሥጋው ቁርበት ላይ አሮጌ ለምጽ ነው፥ ካህኑም፦ ርኩስ ነው ይለዋል፤ እርሱ ርኩስ ነውና አይዘጋበትም። ምዕራፉን ተመልከት |