Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 12:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ጠቦት ለማ​ም​ጣት የሚ​በቃ ገን​ዘብ በእ​ጅዋ ባይ​ኖ​ራት ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ሌላ​ው​ንም ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ታቀ​ር​ባ​ለች፤ ካህ​ኑም ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ታል፤ እር​ስ​ዋም ትነ​ጻ​ለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ጠቦት ለማምጣት ዐቅሟ ካልፈቀደ፣ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ጫጩቶች፣ አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት፣ ሌላው ደግሞ ለኀጢአት መሥዋዕት ታቅርብ፤ በዚህም ካህኑ ያስተሰርይላታል፤ እርሷም ትነጻለች።’ ”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ጠቦት ለማቅረብ በቂ ገንዘብ ባታገኝ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች ትውሰድ፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውንም ለኃጢአት መሥዋዕት ታድርገው፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፥ እርሷም ትነጻለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 “ሴትዮዋ የበግ ጠቦት ማምጣት ካልቻለች፥ ሁለት ርግቦች ወይም ሁለት ዋኖሶች ታምጣ፤ እነርሱም አንዱ ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውም ስለ ኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ይቀርባሉ፤ ካህኑም ያስተሰርይላትና ትነጻለች፤ ከዚያም በኋላ የነጻች ትሆናለች።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ጠቦት ለማምጣት ገንዘብዋ ያልበቃት እንደ ሆነ ሁለት ዋኖሶች ወይም ሁለት የርግብ ግልገሎች፥ አንዱን ለሚቃጠል መሥዋዕት ሌላውንም ለኃጢአት መሥዋዕት ታቀርባለች፤ ካህኑም ያስተሰርይላታል፥ እርስዋም ትነጻለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 12:8
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የሚ​ያ​ቀ​ር​በው ቍር​ባን የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ከዎ​ፎች ቢሆን፥ ቍር​ባ​ኑን ከዋ​ኖስ ወይም ከር​ግብ ያቀ​ር​ባል።


ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያቀ​ር​በ​ዋል፤ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ላ​ት​ማል፤ ከደ​ም​ዋም ፈሳሽ ትነ​ጻ​ለች። ወንድ ወይም ሴት ለም​ት​ወ​ልድ ሴት ሕጉ ይህ ነው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሙሴ​ንና አሮ​ንን እን​ዲህ ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፦


“ድሃም ቢሆን፥ በእ​ጁም ገን​ዘብ ባይ​ኖ​ረው፥ ማስ​ተ​ስ​ረያ ይሆ​ን​ለት ዘንድ አንድ ጠቦት ስለ በደል የመ​ለ​የት መሥ​ዋ​ዕት፥ ከመ​ስ​ፈ​ሪ​ያ​ውም ከዐ​ሥር እጅ አንድ እጅ የሆነ በዘ​ይት የተ​ለ​ወሰ የስ​ንዴ ዱቄት ለቍ​ር​ባን፥ አንድ ማሰሮ ዘይ​ትም ያመ​ጣል።


ሁለት ዋኖ​ሶች፥ ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች በእጁ እን​ዳ​ገኘ አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ይወ​ስ​ዳል።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዞ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ያመ​ጣል፤ ለካ​ህ​ኑም ይሰ​ጠ​ዋል።


ካህ​ኑም አን​ዲ​ቱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት፥ አን​ዲ​ቱ​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ ካህ​ኑም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ስለ ፈሳሹ ነገር ሁሉ ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል።


በስ​ም​ን​ተ​ኛ​ውም ቀን ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ይዛ ወደ ካህኑ ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ታመ​ጣ​ቸ​ዋ​ለች።


ስቡ​ንም ሁሉ እንደ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት ስብ፥ በመ​ሠ​ዊ​ያው ላይ ይጨ​ም​ረ​ዋል። ካህ​ኑም ኀጢ​አ​ቱን ያስ​ተ​ሰ​ር​ይ​ለ​ታል፤ ኀጢ​አ​ቱም ይቅር ይባ​ል​ለ​ታል።


“ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች ለማ​ም​ጣት ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው፥ ስለ ሠራው ኀጢ​አት የኢፍ መስ​ፈ​ሪያ ዐሥ​ረኛ ክፍል መል​ካም የስ​ንዴ ዱቄት ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ያቀ​ር​ባል፤ የኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ነውና ዘይት አያ​ፈ​ስ​ስ​በ​ትም፤ ዕጣ​ንም አይ​ጨ​ም​ር​በ​ትም።


“ስለ ሠራው ኀጢ​አት የበግ መግዣ ገን​ዘብ በእጁ ባይ​ኖ​ረው ግን፥ ሁለት ዋኖ​ሶች ወይም ሁለት የር​ግብ ግል​ገ​ሎች፥ አን​ዱን ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ሁለ​ተ​ኛ​ው​ንም ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ር​ባል። ወደ ካህ​ኑም ያመ​ጣ​ቸ​ዋል፤


ኢየሱስም ወደ መቅደስ ገባና በመቅደስ የሚሸጡትንና የሚገዙትን ሁሉ አስወጣ፤ የገንዘብ ለዋጮችንም ገበታዎች የርግብ ሻጮችንም ወንበሮች ገለበጠና


የጌ​ታ​ችን የኢ​የ​ሱስ ክር​ስ​ቶ​ስን ቸር​ነ​ቱን ታው​ቃ​ላ​ችሁ፤ በእ​ርሱ ድህ​ነት እና​ንተ ባለ​ጸ​ጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ባለ​ጸጋ ሲሆን፥ ስለ እና​ንተ ራሱን ድሃ አደ​ረገ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች