Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ዘሌዋውያን 12:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ሴት ልጅም ብት​ወ​ልድ እንደ ግዳ​ጅዋ ወራት ሁለት ሳም​ንት ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤ ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ድረስ ስድሳ ስድ​ስት ቀን ትቈይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 ነገር ግን የወለደችው ሴት ልጅ ከሆነ፣ እንደ ወር አበባዋ ጊዜ ሁለት ሳምንት ትረክሳለች፤ ከዚያም ከደሟ እስክትነጻ ስድሳ ስድስት ቀን ትቈይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 ነገር ግን ሴት ልጅ ብትወልድ እንደ ወር አበባዋ ጊዜያት ሁለት ሳምንት ያኽል የረከሰች ትሆናለች፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስልሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 “እንዲሁም አንድ ሴት፥ ሴት ልጅ ብትወልድ፥ በወር አበባዋ ጊዜ በሚደረገው ዐይነት፥ እስከ ዐሥራ አራት ቀን ድረስ የረከሰች ትሆናለች፤ ከዚህም በኋላ ደምዋ እስኪደርቅና የመንጻትዋ ወራት እስኪፈጸም ድረስ ስድሳ ስድስት ቀኖች ትቈይ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 ሴት ልጅም ብትወልድ እንደ መርገምዋ ወራት ሁለት ሳምንት ያህል የረከሰች ናት፤ ከደምዋም እስክትነጻ ድረስ ስድሳ ስድስት ቀን ትቀመጥ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ዘሌዋውያን 12:5
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላ​ክም ሴቲ​ቱን፥ “ይህን ለምን አደ​ረ​ግሽ?” አላት። ሴቲ​ቱም አለች፥ “እባብ አሳ​ተ​ኝና በላሁ።”


“ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች እን​ዲህ ብለህ ተና​ገ​ራ​ቸው፦ ሴት ብታ​ረ​ግዝ ወንድ ልጅም ብት​ወ​ልድ፥ ሰባት ቀን ያህል የረ​ከ​ሰች ናት፤


ከደ​ም​ዋም እስ​ክ​ት​ነጻ ሠላሳ ሦስት ቀን ትቈይ፤ የመ​ን​ጻቷ ቀንም እስ​ኪ​ፈ​ጸም ድረስ የተ​ቀ​ደ​ሰን ነገር አት​ንካ፤ ወደ መቅ​ደ​ስም አት​ግባ።


“የመ​ን​ጻቷ ወራ​ትም በተ​ፈ​ጸመ ጊዜ፥ ለወ​ንድ ልጅ ወይም ለሴት ልጅ፥ የአ​ንድ ዓመት ጠቦት ለሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕት፥ የር​ግ​ብም ግል​ገል ወይም ዋኖስ ለኀ​ጢ​አት መሥ​ዋ​ዕት ወደ ምስ​ክሩ ድን​ኳን ደጃፍ ወደ ካህኑ ታመ​ጣ​ለች።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች