Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 5:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

5 ጠላ​ቶ​ቻ​ችን አሳ​ደ​ዱን፤ እኛም ደክ​መ​ናል፤ ዕረ​ፍ​ትም የለ​ንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

5 የሚያሳድዱን ከተረከዞቻችን ሥር ናቸው፤ ተጨንቀናል ዕረፍትም ዐጥተናል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

5 አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

5 ቀንበር እንደተጫኑ እንስሶች በመነዳት እጅግ ደክመናል፤ እንድናርፍም አይፈቀድልንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

5 አሳዳጆቻችን በአንገታችን ላይ ናቸው፥ እኛ ደክመናል ዕረፍትም የለንም።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 5:5
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “ሰን​ሰ​ለ​ትና ቀን​በር ሥራ፤ በአ​ን​ገ​ት​ህም ላይ አድ​ርግ፤


“ለባ​ቢ​ሎን ንጉ​ሥም ለና​ቡ​ከ​ን​ደ​ነ​ፆር የማ​ይ​ገ​ዛ​ውን፥ ከባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ ቀን​በር በታች አን​ገ​ቱን ዝቅ የማ​ያ​ደ​ር​ገ​ውን ሕዝ​ብና መን​ግ​ሥት፥ ያን ሕዝብ በእጁ እስ​ካ​ጠ​ፋው ድረስ በሰ​ይ​ፍና በራብ፥ በቸ​ነ​ፈ​ርም እቀ​ጣ​ለሁ፥ ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላ​ልና፦ ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ለና​ቡ​ከ​ደ​ነ​ፆር ይገ​ዙ​ለት ዘንድ የብ​ረ​ትን ቀን​በር በእ​ነ​ዚህ አሕ​ዛብ ሁሉ አን​ገት ላይ አድ​ር​ጌ​አ​ለሁ፤ እነ​ር​ሱም ይገ​ዙ​ለ​ታል፤ የም​ድረ በዳ አራ​ዊ​ትን ደግሞ ሰጥ​ቼ​ዋ​ለሁ።”


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ ሰፊው የባ​ቢ​ሎን ቅጥር ፈጽሞ ይፈ​ር​ሳል፤ ረጃ​ጅ​ሞች በሮ​ች​ዋም በእ​ሳት ይቃ​ጠ​ላሉ፤ ሕዝቡ ለከ​ንቱ ይደ​ክ​ማሉ፤ አሕ​ዛ​ብም በመ​ጀ​መ​ሪያ በእ​ሳት ያል​ቃሉ።”


ኖን። በእጄ ስለ​ተ​ታቱ ኀጢ​አ​ቶች ተጋ፤ በአ​ን​ገቴ ላይ ወጥ​ተ​ዋል፤ ጕል​በቴ ደከመ። እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልቋ​ቋ​መው በማ​ል​ች​ለው መከራ እጅ ሰጥ​ቶ​ኛ​ልና።


ጋሜል። ይሁዳ ስለ ውር​ደ​ቷና ስለ ባር​ነቷ ብዛት ተሰ​ደ​ደች፤ በአ​ሕ​ዛብ መካ​ከል ተቀ​መ​ጠች፤ ዕረ​ፍ​ትም አላ​ገ​ኘ​ችም፤ የሚ​ያ​ሳ​ድ​ዱ​አት ሁሉ በሚ​ያ​ስ​ጨ​ን​ቁ​አት መካ​ከል ያዙ​ዋት።


ቆፍ። አሳ​ዳ​ጆ​ቻ​ችን ከሰ​ማይ ንስር ይልቅ ፈጣ​ኖች ሆኑ፤ በተ​ራ​ሮች ላይ አሳ​ደ​ዱን፤ በም​ድረ በዳም ሸመ​ቁ​ብን።


ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ በዚህ ወገን ላይ በክፉ አስባለሁ፥ ከዚያም አንገታችሁን አታነሡም፥ ዘመኑም ክፉ ነውና ቀጥ ብላችሁ አትሄዱም።


ቀንበሬን በላያችሁ ተሸከሙ፤ ከእኔም ተማሩ፤ እኔ የዋህ በልቤም ትሑት ነኝና፤ ለነፍሳችሁም ዕረፍት ታገኛላችሁ፤


አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን አት​ፈ​ታ​ተ​ኑት፤ እኛም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ልን​ሸ​ከ​መው ያል​ቻ​ል​ነ​ውን ቀን​በር በደቀ መዛ​ሙ​ርት ጫንቃ ላይ ለምን ትጭ​ና​ላ​ችሁ?


በራ​ብና በጥ​ማት፥ በዕ​ራ​ቁ​ት​ነ​ትም፥ ሁሉ​ንም በማ​ጣት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ለሚ​ል​ክ​ብህ ለጠ​ላ​ቶ​ችህ ትገ​ዛ​ለህ፤ እስ​ኪ​ያ​ጠ​ፋ​ህም ድረስ በአ​ን​ገ​ትህ ላይ የብ​ረት ቀን​በር ይጭ​ናል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች