Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ሰቈቃወ 2:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

12 ላሜድ። በከ​ተማ ጎዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍ​ሳ​ቸ​ውም በእ​ና​ቶ​ቻ​ቸው ብብት እለይ-እለይ ባለች ጊዜ፥ እና​ቶ​ቻ​ቸ​ውን፥ “እህ​ልና ወይን ወዴት አለ?” ይሉ​አ​ቸ​ዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

12 በከተማዪቱ መንገዶች ላይ፣ እንደ ቈሰሉ ሰዎች ሲደክሙ፣ በእናታቸው ክንድ ላይ፣ ነፍሳቸው በመውጣት ላይ ሳለች፣ “ምግብና የወይን ጠጅ የት አለ?” እያሉ እናቶቻቸውን ይጠይቃሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

12 ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

12 በጦር ሜዳ እንደ ቈሰለ ወታደር በከተማው መንገዶች እየተዝለፈለፉ በእናታቸው ክንድ ላይ ሆነው፥ “ምግብና ውሃ!” እያሉ እያለቀሱ፥ ሕይወታቸው ያልፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

12 ላሜድ። በከተማ ጐዳና እንደ ተወጋ ሰው በዛሉ ጊዜ፥ ነፍሳቸውም በእናቶቻቸው ብብት በወጣች ጊዜ፥ እናቶቻቸውን፦ እህልና የወይን ጠጅ ወዴት አለ? ይሉአቸዋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ሰቈቃወ 2:12
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አሁ​ንም ነፍሴ በው​ስጤ ፈሰ​ሰች፤ ጭን​ቀ​ትም በእኔ ላይ ሞላ፤


ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ ጐል​ማ​ስ​ነ​ቴ​ንም ደስ ወዳ​ሰ​ኛት ወደ አም​ላኬ እገ​ባ​ለሁ፤ አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ በመ​ሰ​ንቆ አመ​ሰ​ግ​ን​ሃ​ለሁ።


ነፍሴ በኋ​ላህ ተከ​ታ​ተ​ለች፥ እኔ​ንም ቀኝህ ተቀ​በ​ለ​ችኝ።


ልጆ​ችሽ ዝለ​ዋል፤ እንደ ጠወ​ለገ ቅጠ​ልም በየ​መ​ን​ገዱ ዳር ወድ​ቀ​ዋል፤ በአ​ም​ላ​ክሽ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቍጣና ተግ​ሣጽ ተሞ​ል​ተ​ዋል።


ስለ​ዚ​ህም እርሱ ብዙ​ዎ​ችን ይወ​ር​ሳል፤ ከኀ​ያ​ላ​ንም ጋር ምር​ኮን ይከ​ፋ​ፈ​ላል፤ ነፍ​ሱን ለሞት አሳ​ልፎ ሰጥ​ቶ​አ​ልና፥ ከዐ​መ​ፀ​ኞ​ችም ጋር ተቈ​ጥ​ሮ​አ​ልና፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎ​ችን ኀጢ​አት ተሸ​ከመ፤ ስለ ኀጢ​አ​ታ​ቸ​ውም ተሰጠ።


መከ​ር​ህ​ንና እን​ጀ​ራ​ህን ይበ​ላሉ፤ ወን​ዶ​ችና ሴቶች ልጆ​ች​ህ​ንም ይበ​ሉ​አ​ቸ​ዋል፤ በጎ​ች​ህ​ንና ላሞ​ች​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ ወይ​ን​ህ​ንና በለ​ስ​ህ​ንም፥ ዘይ​ት​ህ​ንም ይበ​ላሉ፤ የም​ት​ታ​መ​ና​ቸ​ውን የተ​መ​ሸጉ ከተ​ሞ​ች​ህ​ንም በሰ​ይፍ ያጠ​ፋሉ።”


ካፍ። ሕዝ​ብዋ ሁሉ እን​ጀራ አጥ​ተው ያለ​ቅ​ሳሉ፤ ሰው​ነ​ታ​ቸ​ውን ለማ​በ​ር​ታት ፍላ​ጎ​ታ​ቸ​ውን ስለ መብል ሰጥ​ተ​ዋል፤ አቤቱ! ተጐ​ሳ​ቍ​ያ​ለ​ሁና እይ፤ ተመ​ል​ከ​ትም።


ዳሌጥ። ጡት የሚ​ጠ​ባው የሕ​ፃን ምላስ ከጥም የተ​ነሣ ወደ ትና​ጋው ተጣ​በቀ፤ ሕፃ​ናት እን​ጀራ ለመኑ፤ የሚ​ቈ​ር​ስ​ላ​ቸ​ውም የለም።


የባ​ቢ​ሎ​ን​ንም ንጉሥ ክንድ አበ​ረ​ታ​ለሁ፤ ሰይ​ፌ​ንም በእጁ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ግብ​ፅ​ንም ይወ​ጋ​በ​ታል፥ ምር​ኮ​ዋ​ንም ይማ​ር​ካል፤ ሰለ​ባ​ዋ​ንም ይሰ​ል​ባል።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች