ሰቈቃወ 1:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)5 ሄ። ስለ ኀጢአቷ ብዛት እግዚአብሔር አዋርዶአታልና የሚዘባበቱባት በራስዋ ላይ ሆኑ፤ ጠላቶችዋም ተደሰቱ፤ ሕፃናቶችዋም በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። ምዕራፉን ተመልከትአዲሱ መደበኛ ትርጒም5 ባላጋሮቿ ገዦቿ ሆኑ፤ ጠላቶቿ ተመችቷቸዋል፤ ከኀጢአቷ ብዛት የተነሣ፣ እግዚአብሔር ከባድ ሐዘን አምጥቶባታል። ልጆቿ በጠላት ፊት ተማርከው፣ ወደ ግዞት ሄደዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)5 ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። ምዕራፉን ተመልከትአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም5 ከኃጢአትዋ ብዛት የተነሣ እግዚአብሔር ችግር እንዲደርስባት አደረገ፤ ጠላቶችዋ ገዢዎችዋ ሆነዋል፤ ልጆችዋም በጠላት ተማርከው ተወስደዋል ጠላቶችዋ ግን ተሳክቶላቸዋል። ምዕራፉን ተመልከትመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)5 ሄ። ስለ ኃጢአትዋ ብዛት እግዚአብሔር አስጨንቆአታልና አስጨናቂዎችዋ ራስ ሆኑ ጠላቶችዋም ተከናወነላቸው፥ ሕፃናቶችዋ በአስጨናቂዎች ፊት ተማርከዋል። ምዕራፉን ተመልከት |