ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 9:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ሁለተኛውም ዕጣ ወደ ግዮን ማዶ በገነት ቀኝ በሰሜን በኩል ለካም ወጣ፥ ወደ ሰሜንም ይደርሳል። ዋዕይ ወደ ጸናበት ተራራም ሁሉ ይደርሳል፤ በአጤል አንጻር ወዳለ ወደ ምዕራብ ይደርሳል። ወደ ማዕከክ ባሕር እስኪቀርብ ድረስም ወደ ምዕራብ ይደርሳል። ይህችውም የሚጠፋው ሁሉ ወደ እርስዋ የሚወርድባት ሀገር ናት። ወደ ደቡብ ወደ ጋዴት ዳርቻ ይወጣል። ወደ ግዮን ወንዝም እስኪቀርብ ድረስ ወደ ባሕሩ ዳርቻ ወደ ታላቁ ባሕር ይመጣል። ምዕራፉን ተመልከት |