ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 8:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)16 ኖኅም በሃያ ስምንተኛው ኢዮቤልዩ ለልጅ ልጆቹ ሥርዐትንና ትእዛዝን፥ የሚያውቀውንም ፍርድ ሁሉ ያዝዝ ጀመረ። እውነትንም ያደርጉ ዘንድ፥ የሰውነታቸውንም ኀፍረት ይሸፍኑ ዘንድ፥ የፈጠራቸው እግዚአብሔርንም ያመሰግኑ ዘንድ፥ አባትና እናታቸውንም ያከብሩ ዘንድ፥ እያንዳንዳቸውም ባልንጀራቸውን ይወድዱ ዘንድ፥ ሰውነታቸውንም ከዝሙትና ከርኵሰት፥ ከበደልም ይጠብቁ ዘንድ ያዝዛቸው ጀመር። ምዕራፉን ተመልከት |