ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 7:2 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 በሃያ ሰባተኛውም ቀን መርከቢቱን ከፈታት፤ ከውስጥዋም አራዊትንና ወፎችን፥ የሚንቀሳቀሰውንም ሁሉ ሰደደ። በሦስተኛውም ወር መባቻ ኖኅ ከመርከብ ወጣ። በዚህም ተራራ ላይ መሠዊያን ሠራ፤ ለምድርም አስተሰረየ። ከኖኅ ጋር በመርከብ ካሉት በቀር በእርስዋ ያለው ሁሉ ጠፍቶአልና የፍየል ጠቦት ሠውቶ በደሙ የምድርን ኀጢአት ሁሉ አስተሰረየ። ምዕራፉን ተመልከት |