ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 5:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)21 በዐሥረኛው ኢዮቤልዩ በሁለተኛው ሱባዔ መላልኤል ሚስት ትሆነው ዘንድ የአባቱን ወንድም የበራኪሄልን ልጅ ዲናን አገባ። በሦስተኛውም ሱባዔ በስድስተኛው ዓመት ወንድ ልጅን ወለደችለት፥ ስሙንም ያሮድ አለው። በዘመኑ ትጉሃን የተባሉ የእግዚአብሔር መላእክት በምድር የሰው ልጆችን ያስተምሩ ዘንድ፥ በምድርም ፍርድንና ቅንነትን ያደርጉ ዘንድ ወደ ምድር ወርደዋልና። ምዕራፉን ተመልከት |