ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 4:20 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)20 ሔዋንም ዛፉ ያማረ እንደ ሆነ፥ ለማየትም ደስ የሚያሰኝ፥ ፍሬውም ለመብላት የሚያስጐመጅ እንደ ሆነ ባየች ጊዜ ከእርሱ ወስዳ በላች። ኀፍረቷንም በቀደመው በበለሱ ቅጠል ሸፈነች። ለአዳምም ሰጠችውና በላ። ዐይኖቹም አዩ፤ ዕራቁቱንም እንደ ሆነ ባየ ጊዜ የበለስ ቅጠል ወስዶ ሰፋ፤ ግልድም አድርጎም ኀፍረቱን ሸፈነ። ምዕራፉን ተመልከት |