ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 ከልጆቹ ሁሉ ይልቅ ፈጽሞ እርሱን ይወደው ነበርና የጻፋቸውን መጻሕፍት ሁሉ ለታላቁ ልጁ ለሴም ሰጠው። ኖኅም እንደ አባቶቹ ሞተ፤ አራራት በሚባልም ሀገር በሉባር ተቀበረ፤ ኖኅም በሕይወቱ ዘጠኝ መቶ አምሳ ዓመት ጨረሰ። ይህም ዐሥራ ዘጠኝ ኢዮቤልዩ ሁለት ሱባዔና አምስት ዓመት ነው። ፍጹም በሆነባት ሥራው በምድር የኖረው ሕይወቱ ከሄኖክ በቀር ከሰው ልጆች ይልቅ የከበረ ነበር። የሄኖክ ሥራ በፍርድ ቀን የትውልዱን ሁሉ ሥራ ይነግር ዘንድ ለዘለዓለም ትውልድ ምስክር ሊሆን ተፈጥሮአልና። ምዕራፉን ተመልከት |