ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:30 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)30 ከወፎቹም ፊት የተነሣ ዓመቶች ድርቅ ይሆኑ ጀመር፤ የእንጨቱንም ፍሬ ሁሉ ከዛፎቹ ላይ እየለቀሙ ይበሉ ነበር፥ በዘመናቸው ከምድር ፍሬ ሁሉ ጥቂት ማዳን ቢችሉም በታላቅ ኀይል ነበር። በሠላሳ ዘጠነኛውም ኢዮቤልዩ በሁለተኛው ሱባዔ በመጀመሪያው ዓመት ታራ ሚስት አገባ፤ ስምዋም ኤድና ይባላል፤ ይህችውም የአባቱ የእኅት ልጅ የምትሆን የአብራም ልጅ ናት። በዚህም ሱባዔ በሰባተኛው ዓመት ወንድ ልጅን ወለደችለት። የልጁ ልጅ ሳይፀነስ ሙቶአልና ስሙን በእናቱ አባት ስም አብራም አለው። ምዕራፉን ተመልከት |