ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:3 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)3 ኖኅም ወደ ፈጣሪው ወደ እግዚአብሔር እንዲህ ሲል ጸለየ፥ “ምሕረትህን አድርገህ ያዳንኸኝ፥ ልጆችንም ከጥፋት ውኃ ያዳንኻቸው፥ የጥፋትን ልጅ እንዳጠፋኸው እንድጠፋ ያላደረግኸኝ፥ በእኔ ላይ ያለ ይቅርታህ ብዙ ነውና፥ ቸርነትህም በሰውነቴ በዝታለችና፥ በሥጋ ውስጥ ሁሉ ያሉ የነፍሳት ፈጣሪ ሆይ፥ ይቅርታህ በልጆች ላይ ከፍ ከፍ ይበል፤ ክፉዎች አጋንንትም ከዚህ ዓለም እንዳያጠፉአቸው በላያቸው አይሠልጥኑ። ምዕራፉን ተመልከት |