ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:26 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 ስለዚህም ሰው ሁሉ በደልንና ኀጢአትን ሁሉ ወደ መሥራት ተመልሶአልና፥ የሴሩሕ ስም ሴሩግ ተባለ። እርሱም አደገ፤ ለሚስቱም እናት አባት አቅራቢያ በሆነ በከላውዴዎን ዕጣ በዑር ኖረ። ጣዖትንም ያመልክ ነበር፤ እርሱም በሠላሳ ሰባተኛው ኢዮቤልዩ በአምስተኛው ሱባዔ በመጀመሪያው ዓመት ሚስትን አገባ፤ ስምዋም ሜልካ ይባላል፤ ይህችውም የአባቱ የእኅት ልጅ የካቤር ልጅ ናት፥ በዚህ ሱባዔ በመጀመሪያው ዓመት ናኮርን ወለደችለት። ምዕራፉን ተመልከት |