ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:24 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 የኬሴድ ልጅ ዑርም በከላውዴዎን ያለች የዑርን ከተማ ሠራ፤ ስምዋንም በእርሱ ስምና በአባቱ ስም ጠራ። ጣዖቶችንም ሠሩ፤ እያንዳንዱም ለራሱ ቀርፆ ለሠራው ጣዖት ይሰግድ ነበር፤ ጣዖትንና ምስልን፥ ርኵሰትንም ይሠሩ ጀመር፤ ክፉዎች አጋንንትም ኀጢአትንና ርኵሰትን ይሠሩ ዘንድ ይረዱና ያስቱ ነበር። ምዕራፉን ተመልከት |