ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)23 በዚህ ኢዮቤልዩ በሰባተኛው ሱባዔ የኖኅ ልጆች ሰውን ለመማረክና ለመግደል፥ እያንዳንዱም ወንድሙን ለመግደል፥ የሰውንም ደም በምድር ላይ ለማፍሰስ፥ ደምንም ለመብላት፥ የጸኑ ከተማዎችንና አንባዎችን፥ ግንቦችንም ለመሥራት ሕዝብ በሕዝብ ላይ ለመነሣት፥ በመንግሥትም ላይ አስቀድሞ ለመሾም፥ ሕዝቡ በሕዝቡ ፊት፥ አሕዛቡም በአሕዛቡ ፊት ወደ ሰልፍ ለመሄድ፥ ከተማም ከከተማ ጋር ለመጣላት፥ ሁሉም ክፉ ሥራ ለመሥራት፥ የጦር መሣሪያንም ለመግዛት፥ ለልጆቻቸውም ሰልፍን ለማስተማር መዋጋት ጀመሩ። አንዱ አገር ሌላውን አገር ይማርክ፥ ሴት ባሪያንና ወንድ ባሪያንም ይገዙ ጀመር። ምዕራፉን ተመልከት |