ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:19 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)19 ለሴምና ለልጆቹ በዕጣቸው ወጥቶአልና በሴም ሀገር አትኑር፤ አንተም የተረገምህ ነህ። በአባታችን በኖኅና በቅዱሱ ፈራጅ ፊት ለመርገም በመሐላ ከተዘጋጀን ከኖኅ ልጆች ሁሉ ተለይተህ አንተ የተረገምህ ትሆናለህ” አሉት። እርሱ ግን አልሰማቸውም፤ ከኤማት ጀምሮ እስከ ግብፅ መግቢያ ድረስ በሊባኖስ ሀገር ኖረ፤ ልጆቹም እስከዚህ ቀን ድረስ በዚያ ኖሩ። ስለዚህ ያች ሀገር የከነዓን ሀገር ተባለች። ምዕራፉን ተመልከት |