ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 10:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 በሠላሳ ሦስተኛው ኢዮቤልዩ ከሁለተኛው ሱባዔ በመጀመሪያው ዓመት ፋሌክ ስምዋ ሎምና የሚባል ሚስትን አገባ፤ ይህችውም የሴናዖር ልጅ ናት። በዚሁም ሱባዔ በአራተኛው ዓመት ወንድ ልጅን ወለደችለት። ከአራራት ምድር ወደ ምሥራቅ ወደ ሰናዖር ሀገር ስለ ተሰደዱ በሰናዖር ሀገር ከተማንና አምባን ይሠሩ ዘንድ የሰው ልጆች በጽኑ ምክር እነሆ፥ ክፉዎችን ሆኑ ብሎአልና ስሙን ራግው አለው። ወደ ሰማይ እንወጣበታለን ሲሉ በዘመኑ ከተማንና ግንብን ሠርተዋልና፤ መሥራትም ጀምረዋልና። ምዕራፉን ተመልከት |