ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 1:9 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)9 “ብዙ ሰዎች ይጠፋሉ፥ ተይዘውም በጠላቶቻቸው እጅ ይወድቃሉ። ሥርዐቴንና ትእዛዜን፥ የቃል ኪዳኔንም በዓላት፥ ሰንበታትንም፥ በመካከላቸውም የለየሁትን ቅድሳቴን፤ ስሜ በእርሱ ይጠራ ዘንድ፥ ያድርበትም ዘንድ በምድር መካከል ያከበርሁትን ድንኳኔንና መቅደሴን ትተዋልና። ምዕራፉን ተመልከት |