ይህ መፅሐፍ በእግዚአብሔር አልተነፀረም እና የክርስቲያን ካኖን ወይም የአይሁድ ታናክ ክፍል አይደለም። ለታሪክና ለጥናት ዓላማ ብቻ ይታያል። ሙሉ ማብራሪያን ይመልከቱ መጽሐፈ ኩፋሌ 1:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 አንተም እኔ ዛሬ የነገርሁህን ይህን ሁሉ ነገር ጻፍ። እኔ ቍጣቸውን አውቃለሁና፥ ማርና ወተትን የምታስገኝ ሀገርን ለልጆቻችሁ እሰጣለሁ ብዬ ለአብርሃምና ለይስሐቅ ለያዕቆብም ወደማልሁላቸው ሀገር ሳላገባቸው አንገታቸው ደንዳና እንደ ሆነ አውቃለሁና፥ በልተውና ጠግበው ከመከራቸው ሁሉ ወደማያድናቸው ወደ ልዩ ጣዖት ይመለሳሉና። ምዕራፉን ተመልከት |