Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 9:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 አለ​ቆ​ቹም “አዳ​ን​ና​ችሁ፤ ለማ​ኅ​በ​ሩም እን​ጨት ትቈ​ር​ጡና ውኃ ትቀዱ ዘንድ መደ​ብ​ና​ችሁ” አሉ​አ​ቸው። አለ​ቆ​ቹም እን​ዲሁ አዘ​ዙ​አ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ነገር ግን ለማኅበረ ሰቡ በሙሉ ዕንጨት እየቈረጡ ውሃ እየቀዱ ይኑሩ።” ስለዚህ መሪዎቹ የገቡላቸው ቃል ተጠበቀ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 አለቆቹም፦ “በሕይወት ይኑሩ” አሉአቸው፤ አለቆቹም እንደ ተናገሩአቸው ለማኅበሩ ሁሉ እንጨት ቆራጮች ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 መሪዎቹም ስለ እነርሱ በወሰኑት መሠረት፦ ይኑሩ፤ ነገር ግን ለመላው ማኅበር እንጨት በመልቀምና ውሃ በመቅዳት ያገልግሉ” አሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 አለቆቹም፦ በሕይወት ይኑሩ አሉአቸው፥ አለቆቹም እንደ ተናገሩአቸው ለማኅበሩ ሁሉ እንጨት ቆራጮች ውኃም ቀጂዎች ሆኑ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 9:21
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሠራ​ዊ​ትም በኀ​ይል ይዘ​ም​ቱ​ባ​ታ​ልና፥ እንደ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችም በም​ሳር ይመ​ጡ​ባ​ታ​ልና ድም​ፅዋ እን​ደ​ም​ት​ሸሽ እባብ ይተ​ማል።


ሁላ​ችሁ፥ የነ​ገ​ዶ​ቻ​ችሁ አለ​ቆች ሽማ​ግ​ሌ​ዎ​ቻ​ች​ሁም፥ ሹሞ​ቻ​ች​ሁም፥ ጻፎ​ቻ​ች​ሁም፥ የእ​ስ​ራ​ኤል ወንድ ሁሉ ዛሬ በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ፊት ቆማ​ች​ኋል።


ሴቶ​ቻ​ች​ሁም፥ ልጆ​ቻ​ች​ሁም ከእ​ን​ጨት ለቃ​ሚ​ያ​ችሁ እስከ ውኃ ቀጃ​ችሁ በሰ​ፈ​ራ​ችሁ ያለ መጻ​ተኛ፤


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥


ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።


ስለ​ማ​ል​ን​ላ​ቸው መሐላ ጥፋት እን​ዳ​ይ​ሆ​ን​ብን ይህን አና​ድ​ር​ግ​ባ​ቸው፤ በሕ​ይ​ወ​ትም እን​ተ​ዋ​ቸው፤ እን​ግ​ዛ​ቸ​ውም” አሉ​አ​ቸው።


አሁ​ንም የተ​ረ​ገ​ማ​ችሁ ሁኑ፤ ለእ​ኔም፥ ለአ​ም​ላ​ኬም እን​ጨት ቈራጭ፥ ውኃም ቀጂ የሆነ ባሪያ ከእ​ና​ንተ አይ​ጠ​ፋም” አላ​ቸው።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች