Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 9:15 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

15 ኢያ​ሱም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ሰላም አደ​ረገ፤ በሕ​ይ​ወት እን​ዲ​ተ​ዋ​ቸ​ውም ከእ​ነ​ርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደ​ረገ፤ የማ​ኅ​በ​ሩም አለ​ቆች ማሉ​ላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

15 ኢያሱም በሰላም ለመኖር የሚያስችላቸውን ቃል ኪዳን ከእነርሱ ጋራ አደረገ፤ የጉባኤውም መሪዎች ይህንኑ በመሐላ አጸኑላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

15 ኢያሱም ከእነርሱ ጋር የሰላም ስምምነት አደረገ፥ በሕይወት እንዲኖሩም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፤ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

15 ስለዚህም ኢያሱ ከእነርሱ ጋር ለሕይወታቸው ዋስትና ቃል ኪዳን በመግባት የሰላም ስምምነት አደረገ። የእስራኤል ሕዝብ መሪዎችም ስምምነቱን ለመጠበቅ ቃል ገቡላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

15 ኢያሱም ከእነርሱ ጋር ሰላም አደረገ፥ በሕይወት እንዲተዋቸውም ከእነርሱ ጋር ቃል ኪዳን አደረገ፥ የማኅበሩም አለቆች ማሉላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 9:15
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉሡ ዳዊ​ትም የገ​ባ​ዖ​ንን ሰዎች ጠራ፤ የገ​ባ​ዖን ሰዎ​ችም ከአ​ሞ​ራ​ው​ያን የተ​ረፉ ነበሩ እንጂ ከእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ወገን አል​ነ​በ​ሩም፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ምለ​ው​ላ​ቸው ነበር፤ ሳኦል ግን ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆ​ችና ለይ​ሁዳ ስለ ቀና ሊገ​ድ​ላ​ቸው ወድዶ ነበር።


በገ​ባ​ዖን ከሚ​ኖሩ ከኤ​ዎ​ና​ው​ያን በቀር፤ እስ​ራ​ኤል ያል​ያ​ዙት ከተማ አል​ነ​በ​ረም፥ ሁሉን በጦ​ር​ነት ያዙ።


ከእ​ነ​ር​ሱና ከአ​ማ​ል​ክ​ቶ​ቻ​ቸው ጋር ቃል ኪዳን አታ​ድ​ርግ።


ከእ​ነ​ር​ሱም ጋር ቃል ኪዳን ካደ​ረጉ ከሦ​ስት ቀን በኋላ ከቅ​ርብ እን​ደ​ሆ​ኑና በአ​ጠ​ገ​ባ​ቸው እን​ደ​ሚ​ኖሩ ሰሙ።


እን​ዲ​ህም ሆነ፤ የኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ንጉሥ አዶ​ኒ​ቤ​ዜቅ ኢያሱ ጋይን እንደ ያዘ፥ ፈጽ​ሞም እን​ዳ​ጠ​ፋት፥ በኢ​ያ​ሪ​ኮና በን​ጉ​ሥ​ዋም ያደ​ረ​ገ​ውን እን​ዲሁ በጋ​ይና በን​ጉ​ሥ​ዋም እን​ዳ​ደ​ረገ፥ የገ​ባ​ዖ​ንም ሰዎች ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤል ጋር ሰላም እን​ዳ​ደ​ረጉ፥ በመ​ካ​ከ​ላ​ቸ​ውም እንደ ሆኑ በሰማ ጊዜ፥


“ወደ እኔ ኑ፤ ከኢ​ያ​ሱና ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ጋር ሰላም አድ​ር​ገ​ዋ​ልና ገባ​ዖ​ንን ለመ​ው​ጋት አግ​ዙኝ” አለ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች