Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እን​ዲ​ህም ብሎ አዘ​ዛ​ቸው፥ “እነሆ፥ ሂዱና ከከ​ተ​ማ​ዪቱ በስ​ተ​ኋላ ተደ​በቁ፤ ከከ​ተ​ማ​ዪቱ አት​ራቁ፤ ሁላ​ች​ሁም ተዘ​ጋ​ጅ​ታ​ችሁ ተቀ​መጡ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እንዲህ የሚል ትእዛዝም ሰጣቸው፤ “እነሆ፤ ከከተማዪቱ በስተጀርባ ታደፍጣላችሁ፤ ከከተማዪቱ አትራቁ፤ ሁላችሁም ነቅታችሁ ተጠባበቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ “እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፤ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ነቅታችሁ ጠብቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እንዲህ የሚል ትእዛዝ ሰጣቸው፦ “ከከተማይቱ በስተኋላ አድፍጣችሁ ቈዩ፤ ይሁን እንጂ ከከተማይቱ ብዙ ሳትርቁ አደጋ ለመጣል በሚያስችላችሁ ሁኔታ ተዘጋጅታችሁ ጠብቁ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እንዲህም ብሎ አዘዛቸው፦ እነሆ፥ ከከተማይቱ በስተ ኋላ ተደበቁ፥ ከከተማይቱ አትራቁ፥ ሁላችሁም ተዘጋጁ፥

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:4
14 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ንጉ​ሡም በሌ​ሊት ተነ​ሥቶ ብላ​ቴ​ኖ​ቹን፥ “ሶር​ያ​ው​ያን ያደ​ረ​ጉ​ብ​ንን እነ​ግ​ራ​ች​ኋ​ለሁ፤ እንደ ተራ​ብን ያው​ቃሉ፤ ስለ​ዚህ፦ ከከ​ተ​ማ​ይቱ በወጡ ጊዜ በሕ​ይ​ወ​ታ​ቸው እን​ይ​ዛ​ቸ​ዋ​ለን፤ ወደ ከተ​ማም እን​ገ​ባ​ለን ብለው በሜዳ ይሸ​ሸጉ ዘንድ ከሰ​ፈሩ ወጥ​ተ​ዋል” አላ​ቸው።


ኢዮ​ር​ብ​ዓም ግን በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ይመ​ጣ​ባ​ቸው ዘንድ ድብቅ ጦር አዞ​ረ​ባ​ቸው፤ እነ​ርሱ በይ​ሁዳ ሰፈር ፊት ሳሉ ድብቅ ጦሩ በስ​ተ​ኋ​ላ​ቸው ከበ​ባ​ቸው።


በከ​ተማ ከሚ​ኖሩ ዐሥር ገዢ​ዎች ይልቅ ጥበብ ጠቢ​ብን ትረ​ዳ​ዋ​ለች።


እኔም፥ “ከኀ​ይል ይልቅ ጥበብ ትበ​ል​ጣ​ለች፤ የድ​ሃው ጥበብ ግን ተና​ቀች ቃሉም አል​ተ​ሰ​ማ​ችም” አልሁ።


አንተ ግን እሽ አት​በ​ላ​ቸው፤ ሊገ​ድ​ሉት ሽም​ቀ​ዋ​ልና፤ እስ​ኪ​ገ​ድ​ሉ​ትም ድረስ እን​ዳ​ይ​በ​ሉና እን​ዳ​ይ​ጠጡ እን​ዲህ የተ​ማ​ማሉ ሰዎች ከአ​ርባ ይበ​ዛሉ፤ አሁ​ንም እስ​ክ​ት​ል​ክ​ላ​ቸው ይጠ​ብ​ቃሉ እንጂ እነ​ርሱ ቈር​ጠ​ዋል።”


የሀ​ገ​ሪ​ቱም ሰዎች ሁሉ ተጠሩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ተከ​ት​ለው አሳ​ደ​ዱ​አ​ቸው፤ ከከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም እን​ዲ​ርቁ አደ​ረ​ጓ​ቸው።


ኢያ​ሱም፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ቹም ሕዝብ ሁሉ ተነ​ሥ​ተው ወደ ጋይ ወጡ፤ ኢያ​ሱም ጽኑ​ዓን፥ ተዋ​ጊ​ዎ​ችና ኀያ​ላን የሆ​ኑ​ትን ሠላሳ ሺህ ሰዎች መረጠ፤ በሌ​ሊ​ትም ላካ​ቸው።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ልጆች ገባ​ዖ​ንን የሚ​ከ​ብ​ቡ​አት ሰዎ​ችን በዙ​ሪ​ያዋ አኖ​ሩ​ባት።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ሰዎች ሁሉ ከስ​ፍ​ራ​ቸው ተነ​ሥ​ተው በበ​ዓ​ል​ታ​ምር ተዋጉ። ከእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አድ​ፍ​ጠው የነ​በ​ሩት ከስ​ፍ​ራ​ቸው ከገ​ባ​ዖን ምዕ​ራብ ወጡ።


የብ​ን​ያም ልጆ​ችም እንደ ተመቱ አዩ፤ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ግን በገ​ባ​ዖን ላይ ባኖ​ሩት ድብቅ ጦር ታም​ነ​ዋ​ልና ለብ​ን​ያም ስፍራ ለቀ​ቁ​ላ​ቸው።


የሰ​ቂ​ማም ሰዎች በተ​ራ​ሮች ራስ ላይ ድብቅ ጦር አደ​ረጉ፤ መን​ገድ ተላ​ላ​ፊ​ዎ​ች​ንም ሁሉ ይዘ​ርፉ ነበር፤ ለአ​ቤ​ሜ​ሌ​ክም ይህን አወ​ሩ​ለት።


አሁ​ንም አን​ተና ከአ​ንተ ጋር ያሉት ሕዝብ በሌ​ሊት ተነሡ፤ በሜ​ዳም ሸምቁ፤


የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እስ​ራ​ኤል ከግ​ብፅ በወጡ ጊዜ በመ​ን​ገድ እንደ ተዋጉ በእ​ስ​ራ​ኤል ላይ ክፉ ያደ​ረ​ጉ​ትን አማ​ሌ​ቃ​ው​ያ​ንን ዛሬ እበ​ቀ​ላ​ለሁ።


ሳኦ​ልም ወደ አማ​ሌቅ ከተማ ወጣ፤ በሸ​ለ​ቆ​ውም ውስጥ ተደ​በቀ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች