Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 8:31 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ጋይ ሙሴ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ልጆች እን​ዳ​ዘዘ፥ በሙ​ሴም ሕግ መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው፥ መሠ​ዊ​ያው ካል​ተ​ወ​ቀ​ረና ብረት ካል​ነ​ካው ድን​ጋይ ነበረ፤ በእ​ር​ሱም ላይ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት አቀ​ረበ፤ የደ​ኅ​ን​ነ​ት​ንም መሥ​ዋ​ዕት ሠዋ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 መሠዊያውንም የሠራው የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ፣ እስራኤላውያንን ባዘዛቸው መሠረት ሲሆን፣ ይህንም የሠራው በሙሴ የሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና የብረት መሣሪያ ባልነካው ድንጋይ ነው፤ በዚህም ላይ የሚቃጠል መሥዋዕት አቀረቡ፤ የኅብረት መሥዋዕትም ሠዉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 የጌታ ባርያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደተጻፈው፥ “መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ”፤ በእርሱም ላይ ለጌታ የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የአንድነትንም መሥዋዕት ሠዉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የእግዚአብሔር አገልጋይ ሙሴ እስራኤላውያንን ባዘዘው መሠረት በሙሴ አማካይነት በተሰጠው የሕግ መጽሐፍ ውስጥ እንደ ተጻፈው ባልተጠረበና ብረት ባልነካው ድንጋይ መሠዊያ ሠርተው የሚቃጠል መሥዋዕትና የአንድነት ቊርባን አቀረቡ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 የእግዚአብሔር ባሪያ ሙሴ የእስራኤልን ልጆች እንዳዘዘ፥ በሙሴም ሕግ መጽሐፍ እንደ ተጻፈው፥ መሠዊያው ካልተወቀረና ብረት ካልነካው ድንጋይ ነበረ፥ በእርሱም ላይ ለእግዚአብሔር የሚቃጠለውን መሥዋዕት አቀረቡ፥ የደኅንነትንም መሥዋዕት ሠዉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 8:31
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በሙሴ ሕግ መጽ​ሐ​ፍም እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሁሉ በኀ​ጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች ስለ ልጆች አይ​ሙቱ፤ ልጆ​ችም ስለ አባ​ቶች አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ የነ​ፍሰ ገዳ​ዮ​ቹን ልጆች አል​ገ​ደ​ላ​ቸ​ውም።


ታላቁ ካህ​ንም ኬል​ቅ​ያስ ጸሓ​ፊ​ውን ሳፋ​ንን፥ “የሕ​ጉን መጽ​ሐፍ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት አግ​ኝ​ቻ​ለሁ” አለው፤ ኬል​ቅ​ያ​ስም መጽ​ሐ​ፉን ለሳ​ፋን ሰጠው፥ እር​ሱም አነ​በ​በው።


እንደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ሕግ ቃል ኪዳን እንደ ተጻፈ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም፥ “ሰው ሁሉ በገዛ ኀጢ​አቱ ይሙት እንጂ አባ​ቶች በል​ጆ​ቻ​ቸው፥ ልጆ​ችም በአ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ፋንታ አይ​ሙቱ” ብሎ እን​ዳ​ዘዘ ልጆ​ቻ​ቸ​ውን ግን አል​ገ​ደ​ለም።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻፈ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያቀ​ርቡ ዘንድ በየ​አ​ባ​ቶ​ቻ​ቸው ቤቶች እንደ ክፍ​ላ​ቸው ለሕ​ዝቡ ልጆች እን​ዲ​ሰጡ የሚ​ቃ​ጠ​ለ​ውን መሥ​ዋ​ዕት ለዩ። እን​ዲ​ሁም በበ​ሬ​ዎቹ አደ​ረጉ።


በሙ​ሴም መጽ​ሐፍ እንደ ተጻ​ፈው በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ባለው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አገ​ል​ግ​ሎት ላይ ካህ​ና​ቱን በየ​ማ​ዕ​ር​ጋ​ቸው፥ ሌዋ​ው​ያ​ኑ​ንም በየ​ክ​ፍ​ላ​ቸው አቆሙ።


በዚ​ያም ቀን የሙ​ሴን መጽ​ሐፍ በሕ​ዝቡ ጆሮ አነ​በቡ፤ አሞ​ና​ው​ያ​ንና ሞዓ​ባ​ው​ያ​ንም ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ጉባኤ ለዘ​ለ​ዓ​ለም እን​ዳ​ይ​ገቡ የሚል በዚያ አገኙ።


የሙሴ አማት ዮቶ​ርም የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንና ሌላ መሥ​ዋ​ዕ​ትን ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወሰደ፤ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ፊት ከሙሴ አማት ጋር እን​ጀራ ሊበሉ አሮ​ንና የእ​ስ​ራ​ኤል ሽማ​ግ​ሌ​ዎች ሁሉ መጡ።


የእ​ስ​ራ​ኤ​ል​ንም ልጆች ጐል​ማ​ሶች ላከ፤ የሚ​ቃ​ጠል መሥ​ዋ​ዕ​ት​ንም አቀ​ረቡ፤ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ስለ ደኅ​ን​ነት መሥ​ዋ​ዕት በሬ​ዎ​ችን ሠዉ።


ሰይጣንም ሰይጣንን የሚያወጣ ከሆነ፥ እርስ በርሱ ተለያየ፤ እንግዲህ መንግሥቱ እንዴት ትቆማለች?


አም​ላ​ካ​ችሁ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ወደ​ሚ​ሰ​ጣ​ችሁ ምድር ዮር​ዳ​ኖ​ስን በተ​ሻ​ገ​ራ​ችሁ ጊዜ ታላ​ላቅ ድን​ጋ​ዮ​ችን ለእ​ና​ንተ አቁሙ፤ በኖ​ራም ምረ​ጓ​ቸው።


የዚ​ህ​ንም ሕግ ቃሎች ሁሉ የተ​ገ​ለጠ አድ​ር​ገህ በድ​ን​ጋ​ዮቹ ላይ ጻፍ።”


የዚህ ሕግ መጽ​ሐፍ ከአ​ፍህ አይ​ለይ፤ ነገር ግን የተ​ጻ​ፈ​በ​ትን ሁሉ ትጠ​ብ​ቅና ታደ​ርግ ዘንድ በቀ​ንም በሌ​ሊ​ትም አን​ብ​በው፤ የዚ​ያን ጊዜም መን​ገ​ድህ ይቀ​ና​ል​ሃል፤ አስ​ተ​ዋ​ይም ትሆ​ና​ለህ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች