Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 6:16 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

16 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ በዞ​ሩና ካህ​ናቱ ቀንደ መለ​ከ​ቱን በነፉ ጊዜ፤ ኢያሱ ለእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አለ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰጥ​ቶ​አ​ች​ኋ​ልና ጩኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

16 በሰባተኛው ዙር ላይ ካህናቱ መለከቱን ሲነፉ፣ ኢያሱ ሕዝቡን እንዲህ ሲል አዘዘ፤ “እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ሰጥቷችኋልና ጩኹ

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

16 በሰባተኛውም ጊዜ ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን እንዲህ አለ፦ “ጌታ ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

16 በሰባተኛው ዙር ካህናቱ እምቢልታ ሊነፉ በሚዘጋጁበት ጊዜ ኢያሱ ሕዝቡን፦ “እግዚአብሔር ከተማይቱን ስለ ሰጣችሁ ጩኹ!” ብሎ አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

16 በሰባተኛውም ጊዜ ካህናቱ ቀንደ መለከቱን ሲነፉ ኢያሱ ሕዝቡን አለ፦ እግዚአብሔር ከተማይቱን ሰጥቶአችኋልና ጩኹ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 6:16
6 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ጮኹ፤ የይ​ሁ​ዳም ሰዎች በጮኹ ጊዜ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ኢዮ​ር​ብ​ዓ​ም​ንና እስ​ራ​ኤ​ልን ሁሉ በይ​ሁዳ ንጉሥ በአ​ብ​ያና በሕ​ዝቡ ፊት መታ​ቸው።


ቀንደ መለ​ከ​ቱም ባለ​ማ​ቋ​ረጥ ሲነፋ፥ የመ​ለ​ከ​ቱን ድምፅ ስት​ሰሙ፥ ሕዝቡ ሁሉ ታላቅ ጩኸት ይጩኹ፤ የከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ቅጥር ይወ​ድ​ቃል፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ እያ​ን​ዳ​ንዱ ፊት ለፊት እየ​ሮጠ ይገ​ባ​ባ​ታል።”


በሰ​ባ​ተ​ኛ​ውም ቀን በነጋ ጊዜ ማል​ደው ተነሡ፤ እን​ደ​ዚ​ህም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ፤ በዚ​ያም ቀን ብቻ ከተ​ማ​ዪ​ቱን ሰባት ጊዜ ዞሩ።


የይ​ሁ​ዳም ሰዎች ወደ ኋላ​ቸው በተ​መ​ለ​ከቱ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሰልፉ በፊ​ታ​ቸ​ውና በኋ​ላ​ቸው ነበረ፤ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ጮኹ፤ ካህ​ና​ቱም መለ​ከ​ቱን ነፉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች