Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 6:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፦ እን​ዳ​ይ​ጮኹ ማንም ድም​ፃ​ቸ​ውን እን​ዳ​ይ​ሰማ፥ እን​ዲ​ጮኹ እስ​ኪ​ያ​ዛ​ቸ​ውም ድረስ ከአ​ፋ​ቸው ቃል እን​ዳ​ይ​ወጣ አዘ​ዛ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 ኢያሱ ሕዝቡን፣ “የማሸበሪያ ጩኸት አታሰሙ፤ ድምፃችሁ ከፍ ብሎ አይሰማ፤ ጩኹ እስከምላችሁም ቀን ድረስ ከአፋችሁ አንዲት ቃል አትውጣ፤ የምትጮኹት ከዚያ በኋላ ነው” ሲል አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ኢያሱም ሕዝቡን እንዲህ ብሎ አዘዛቸው፦ “እኔ፦ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ድምፃችሁንም አታሰሙ፥ ከአፋችሁም አንድ ቃል አይውጣ፤ ከዚያን በኋላ ግን ትጮኻላችሁ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ኢያሱ ግን፦ “ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ እንዳትጮኹ፤ ወይም ድምፃችሁ እንዳይሰማ፤ እንዲያውም አንዲት ቃል እንኳ እንዳትናገሩ፤ ጩኹ ስላችሁ በዚያን ጊዜ ትጮኻላችሁ” ብሎ ሕዝቡን አዘዘ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ኢያሱም ሕዝቡን፦ እኔ፦ ጩኹ እስከምልበት ቀን ድረስ አትጩኹ፥ ድምፃችሁንም አታንሡ፥ ከአፋችሁም አንድ ቃል አይውጣ፥ በዚያን ጊዜ ትጮኻላችሁ ብሎ አዘዛቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 6:10
8 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ስለ​ዚህ ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፥ “እነሆ፥ በጽ​ዮን ድን​ጋ​ይን ለመ​ሠ​ረት አስ​ቀ​ም​ጣ​ለሁ፤ ዋጋው ብዙ የሆ​ነ​ውን፥ የተ​መ​ረ​ጠ​ውን፥ የከ​በ​ረ​ው​ንና መሠ​ረቱ የጸ​ና​ውን የማ​ዕ​ዘን ድን​ጋይ አኖ​ራ​ለሁ፤ በእ​ር​ሱም የሚ​ያ​ምን አያ​ፍ​ርም።


አይ​ጮ​ኽም፤ ቃሉ​ንም አያ​ነ​ሣም፤ ድም​ፁ​ንም በሜዳ አያ​ሰ​ማም።


አይከራከርም፤ አይጮህምም፤ ድምፁንም በአደባባይ የሚሰማ የለም።


እነሆ፥ እኔ የአ​ባ​ቴን ተስፋ ለእ​ና​ንተ እል​ካ​ለሁ፤ እና​ንተ ግን ከአ​ር​ያም ኀይ​ልን እስ​ክ​ት​ለ​ብሱ ድረስ በኢ​የ​ሩ​ሳ​ሌም ከተማ ተቀ​መጡ።”


እር​ሱም መልሶ እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “አብ በገዛ ሥል​ጣኑ የወ​ሰ​ነ​ውን ቀኑ​ንና ዘመ​ኑን ልታ​ውቁ አል​ተ​ፈ​ቀ​ደ​ላ​ች​ሁም።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም የቃል ኪዳኑ ታቦት ሄደች፤ ከተ​ማ​ዪ​ቱ​ንም ዞረች፤ ወደ ሰፈ​ርም ተመ​ልሳ በዚያ አደ​ረች።


ሰል​ፈ​ኞ​ችም ፊት ፊት ይሄዱ ነበር፤ ካህ​ና​ቱም ነጋ​ሪት ይመቱ ነበር፤ ከታ​ቦቱ በኋላ ይከ​ተሉ የነ​በ​ሩ​ትም ቀንደ መለ​ከ​ቱን እየ​ነፉ ይሄዱ ነበር።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች