Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 5:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ልጆ​ቻ​ቸ​ውን በእ​ነ​ርሱ ፋንታ አስ​ነሣ፤ እነ​ዚ​ህ​ንም ኢያሱ ገረ​ዛ​ቸው፤ በመ​ን​ገድ ስለ​ተ​ወ​ለዱ አል​ተ​ገ​ረ​ዙም ነበ​ርና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 ስለዚህ በእነርሱ ምትክ ወንዶች ልጆቻቸውን አስነሣ። እንግዲህ ኢያሱ የገረዛቸው እነዚህን ነበር፤ በጕዞ ላይ ሳሉ ባለመገረዛቸው ከነሸለፈታቸው ነበሩና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፤ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 ኢያሱ የገረዛቸው እግዚአብሔር በእነርሱ ቦታ ያስነሣቸውን ልጆቻቸውን ነው፤ እነርሱ በጉዞ ላይ በነበሩ ጊዜ ስላልተገረዙ ሸለፈታሞች ነበሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ልጆቻቸውን በእነርሱ ፋንታ አስነሣ፥ እነዚህንም ኢያሱ ገረዛቸው፥ በመንገድ ሳሉ ስላልገረዙአቸው ሸለፈታሞች ነበሩና።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 5:7
5 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

የዲና ወን​ድ​ሞች ስም​ዖ​ንና ሌዊም እን​ዲህ አሉ​አ​ቸው፥ “እኅ​ታ​ች​ንን ላል​ተ​ገ​ረዘ ሰው ለመ​ስ​ጠት ይህን ነገር እና​ደ​ርግ ዘንድ አይ​ቻ​ለ​ንም፤ ይህ ነውር ይሆ​ን​ብ​ና​ልና።


ንጥ​ቂያ ይሆ​ናሉ ያላ​ች​ኋ​ቸ​ውን ልጆ​ቻ​ች​ሁን እነ​ር​ሱን አገ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ፤ እና​ን​ተም የና​ቃ​ች​ኋ​ትን ምድር ይወ​ር​ሷ​ታል።


ደግሞ፦ ይማ​ረ​ካሉ ያላ​ች​ኋ​ቸው ልጆ​ቻ​ችሁ፥ ዛሬም መል​ካ​ሙን ከክፉ መለ​የት የማ​ይ​ችሉ ሕፃ​ኖ​ቻ​ችሁ እነ​ርሱ ወደ​ዚያ ይገ​ባሉ፤ ምድ​ሪ​ቱ​ንም ለእ​ነ​ርሱ እሰ​ጣ​ለሁ፤ ይወ​ር​ሱ​አ​ታ​ልም።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ወተ​ትና ማር የም​ታ​ፈ​ስ​ሰ​ውን ምድር ለእኛ ይሰ​ጠን ዘንድ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን የማ​ለ​ላ​ቸ​ውን ምድር እን​ደ​ማ​ያ​ሳ​ያ​ቸው የማ​ለ​ባ​ቸ​ውን፥ ከግ​ብፅ የወጡ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም ቃል ያል​ሰሙ፥ እነ​ዚያ ተዋ​ጊ​ዎች ሁሉ እስ​ኪ​ጠፉ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች አርባ ዓመት በመ​ድ​በራ ምድረ በዳ ይዞሩ ነበር።


በተ​ገ​ረ​ዙም ጊዜ እስ​ኪ​ድኑ ድረስ በሰ​ፈር ውስጥ ተቀ​መጡ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች