Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 4:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 ሕዝ​ቡም ሁሉ አካ​ት​ተው በተ​ሻ​ገሩ ጊዜ ታቦተ ሕጉ ተሻ​ገ​ረች፤ እነ​ዚ​ያም ድን​ጋ​ዮች በፊ​ታ​ቸው ተሻ​ገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሕዝቡ ሁሉ ተሻግረው እንዳበቁ፣ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ፣ ሕዝቡ እያዩአቸው ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ፥ ሕዝቡ እያዩ የጌታ ታቦትና ካህናቱ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሁሉም ተሻግረው ካበቁ በኋላ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት እንደገና ወደ ፊት ቀድመው ሕዝቡን መምራት ጀመሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሕዝቡም ሁሉ ፈጽመው በተሻገሩ ጊዜ፥ ሕዝቡ እያዩ የእግዚአብሔር ታቦትና ካህናቱ ተሻገሩ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 4:11
7 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አሁ​ንም አንተ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የሚ​ሸ​ከ​ሙ​ትን ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ዳር ስት​ደ​ርሱ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውስጥ ቁሙ ብለህ እዘዝ” አለው።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳን ታቦተ ሕግ የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት ከዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በወጡ ጊዜ፥ በእ​ግ​ራ​ቸ​ውም የብስ በረ​ገጡ ጊዜ፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ተወ​ር​ውሮ ወደ ስፍ​ራው ተመ​ለሰ፤ ቀድ​ሞም እንደ ነበረ ሂዶ ዳር እስከ ዳር ሞላ።


የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል በደ​ረቅ መሬት ጸን​ተው ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ፈጽ​መው እስ​ኪ​ሻ​ገሩ ድረስ የእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ሁሉ በደ​ረቅ መሬት ተሻ​ገሩ።


ኢያ​ሱም ለሕ​ዝቡ እን​ዲ​ነ​ግር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያዘ​ዘ​ውን ሁሉ እስ​ኪ​ፈ​ጽም ድረስ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል ቆመው ነበር፤ ሕዝ​ቡም ፈጥ​ነው ተሻ​ገሩ።


ሙሴም እን​ዳ​ዘ​ዛ​ቸው የሮ​ቤል ልጆች፥ የጋ​ድም ልጆች፥ የም​ና​ሴም ነገድ እኩ​ሌታ ታጥ​ቀው በእ​ስ​ራ​ኤል ልጆች ፊት ተሻ​ገሩ።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገ​ራ​ችሁ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም መጣ​ችሁ፤ የኢ​ያ​ሪ​ኮም ሰዎች፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊው፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊው፥ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊው፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊው፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው ተዋ​ጉ​አ​ችሁ፥ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ቸው።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ታ​ችሁ ይሄ​ዳ​ልና፥ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ይሰ​በ​ስ​ባ​ች​ኋ​ልና በች​ኮላ አት​ወ​ጡም፤ በመ​ኮ​ብ​ለ​ልም አት​ሄ​ዱም።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች