Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 3:14 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እን​ዲ​ህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ሊሻ​ገሩ ከየ​ድ​ን​ኳ​ና​ቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት በሕ​ዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ስለዚህ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ለመሻገር ሰፈሩን ለቅቀው ሲወጡ፣ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት ከፊታቸው ቀድመው ሄዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 እንዲህም ሆነ፤ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ሕዝቡ ዮርዳኖስን ለመሻገር ድንኳኑን በነቀሉ ጊዜ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙት ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እንዲህም ሆነ፥ ሕዝቡ ዮርዳኖስን ሊሻገሩ ከየድንኳናቸው በወጡ ጊዜ፥ የቃል ኪዳኑን ታቦት የተሸከሙ ካህናት በሕዝቡ ፊት ይሄዱ ነበር።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 3:14
10 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በው​ስ​ጥ​ዋም የወ​ርቅ ማዕ​ጠ​ን​ትና ሁለ​ን​ተ​ና​ዋን በወ​ርቅ የለ​በ​ጡ​አት፥ የኪ​ዳን ታቦት፥ መና ያለ​ባት የወ​ርቅ መሶ​ብና የለ​መ​ለ​መ​ችው የአ​ሮን በትር፥ የኪ​ዳ​ኑም ጽላት ነበ​ሩ​ባት።


“በበ​ዛ​ችሁ ጊዜ፥ በም​ድ​ርም ላይ በረ​ባ​ችሁ ጊዜ፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤ በዚያ ዘመን፦ የእ​ስ​ራ​ኤል ቅዱስ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት እነ​ኋት አይ​ሉም፤ በል​ባ​ቸ​ውም አያ​ስ​ቧ​ትም፤ በአ​ፋ​ቸ​ውም አይ​ጠ​ሯ​ትም፤ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲ​ህም አይ​ሿ​ትም።


የነ​ዌም ልጅ ኢያሱ ካህ​ና​ቱን ጠርቶ፥ “የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ከሙ፤ ሰባ​ትም ካህ​ናት ሰባት ቀንደ መለ​ከት ወስ​ደው በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ታቦት ፊት ይሂዱ” አላ​ቸው።


ኢያ​ሱም ካህ​ና​ቱን፥ “የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​ማ​ችሁ በሕ​ዝቡ ፊት ሂዱ” ብሎ ተና​ገ​ራ​ቸው፤ ካህ​ና​ቱም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ተሸ​ክ​መው በሕ​ዝቡ ፊት ሄዱ።


ለሕ​ዝ​ቡም እን​ዲህ ብለው ዐወጁ፥ “የአ​ም​ላ​ካ​ች​ሁን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የቃል ኪዳ​ኑን ታቦት ሌዋ​ው​ያ​ንና ካህ​ናት ተሸ​ክ​መ​ውት ባያ​ችሁ ጊዜ፥ ከሰ​ፈ​ራ​ችሁ ተነ​ሥ​ታ​ችሁ ተከ​ተ​ሉት።


“ይህን የሕግ መጽ​ሐፍ ውሰዱ፤ በዚ​ያም በእ​ና​ንተ ላይ ምስ​ክር እን​ዲ​ሆን በአ​ም​ላ​ካ​ችሁ በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቃል ኪዳን ታቦት አጠ​ገብ አኑ​ሩት።


ዮር​ዳ​ኖ​ስ​ንም ተሻ​ገ​ራ​ችሁ፤ ወደ ኢያ​ሪ​ኮም መጣ​ችሁ፤ የኢ​ያ​ሪ​ኮም ሰዎች፥ አሞ​ሬ​ዎ​ና​ዊው፥ ፌር​ዜ​ዎ​ና​ዊው፥ ከነ​ዓ​ና​ዊው፥ ኬጤ​ዎ​ና​ዊው፥ ጌር​ጌ​ሴ​ዎ​ና​ዊው፥ ኤዌ​ዎ​ና​ዊው፥ ኢያ​ቡ​ሴ​ዎ​ና​ዊው ተዋ​ጉ​አ​ችሁ፥ አሳ​ል​ፌም በእ​ጃ​ችሁ ሰጠ​ኋ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች