Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 3:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እነሆ፥ የም​ድር ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የቃል ኪዳኑ ታቦት በፊ​ታ​ችሁ ዮር​ዳ​ኖ​ስን ትሻ​ገ​ራ​ለች።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 እነሆ፤ የምድር ሁሉ ጌታ የቃል ኪዳኑ ታቦት ቀድሟችሁ ወደ ዮርዳኖስ ይገባል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 የምድር ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔር የቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ቀድሞ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ ይሸጋገራል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 እነሆ፥ የምድር ሁሉ ጌታ ቃል ኪዳን ታቦት በፊታችሁ ወደ ዮርዳኖስ ያልፋል።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 3:11
15 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

አቤቱ፥ በሰ​ማ​ይና በም​ድር ያለው ሁሉ የአ​ንተ ነውና ታላ​ቅ​ነ​ትና ኀይል፥ ክብ​ርም፥ ድልና ጽንዕ የአ​ንተ ነው፤ ነገ​ሥ​ታ​ቱና ሕዝቡ ሁሉ በፊ​ትህ ይደ​ነ​ግ​ጣሉ።


የከ​ሰል እሳት እን​ደ​ሚ​ቃ​ጠ​ል​በት ምድጃ ከአ​ፍ​ን​ጫው ጢስ ይወ​ጣል።


አቤቱ፥ አም​ላኬ፥ ወደ አንተ ነፍ​ሴን አነ​ሣ​ለሁ።


ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በመ​ሰ​ንቆ፥ በመ​ሰ​ን​ቆና በዝ​ማሬ ድምፅ ዘምሩ።


ሕዝቤ ሆይ፥ ገዥ​ዎ​ቻ​ችሁ ያስ​ጨ​ን​ቁ​አ​ች​ኋል፤ አስ​ጨ​ና​ቂ​ዎች ሴቶ​ችም በላ​ያ​ችሁ ይሠ​ለ​ጥ​ኑ​ባ​ች​ኋል። ሕዝቤ ሆይ፥ የሚ​ያ​መ​ሰ​ግ​ኑ​አ​ችሁ ያስ​ቱ​አ​ች​ኋል፤ የም​ት​ሄ​ዱ​በ​ት​ንም መን​ገድ ያጠ​ፋሉ።


ፈጣ​ሪሽ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ ስሙም የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነው፤ የእ​ስ​ራ​ኤ​ልም አም​ላክ ታዳ​ጊሽ ነው፤ እር​ሱም በም​ድር ሁሉ እን​ደ​ዚሁ ይጠ​ራል።


የአ​ሕ​ዛብ ንጉሥ ሆይ! በአ​ሕ​ዛብ ጥበ​በ​ኞች ሁሉ መካ​ከል፥ በመ​ን​ግ​ሥ​ታ​ቸ​ውም ሁሉ እንደ አንተ ያለ ስለ​ሌለ፥ ለአ​ንተ ክብር ይገ​ባ​ልና አን​ተን የማ​ይ​ፈራ ማን ነው?


የጽዮን ልጅ ሆይ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ጥፍርሽንም ናስ አደርጋለሁና ተነሺ አሂጂ፥ ብዙ አሕዛብንም ታደቅቂአለሽ፥ ትርፋቸውንም ለእግዚአብሔር፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ ትቀድሻለሽ።


እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የተፈራ ይሆናል፥ የምድርንም አማልክት ሁሉ ያከሳቸዋል፣ በአሕዛብም ደሴቶች ሁሉ ላይ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ በስፍራቸው ሆነው ለእርሱ ይሰግዳሉ።


እግዚአብሔርም በምድር ሁሉ ላይ ይነግሣል፣ በዚያ ቀን እግዚአብሔር አንድ፥ ስሙም አንድ ይሆናል።


እርሱም፦ በምድር ሁሉ ጌታ አጠገብ የቆሙት ሁለቱ የተቀቡት እነዚህ ናቸው አለኝ።


መልአኩም መልሶ፦ እነዚህ በምድር ሁሉ ጌታ ፊት ከቆሙበት ስፍራ የሚወጡ አራቱ የሰማይ ነፋስት ናቸው።


አም​ላ​ክ​ህም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በፊ​ትህ እን​ዲ​ያ​ልፍ ዛሬ ዕወቅ፤ እርሱ የሚ​በላ እሳት ነው፤ እርሱ ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል፤ በፊ​ት​ህም ያዋ​ር​ዳ​ቸ​ዋል፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም እንደ ነገ​ረህ ከፊ​ትህ ያር​ቃ​ቸ​ዋል፥ ፈጥ​ኖም ያጠ​ፋ​ቸ​ዋል።


እን​ዲ​ህም ይሆ​ናል፤ የም​ድ​ርን ሁሉ ጌታ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ታቦት የተ​ሸ​ከሙ ካህ​ናት እግር ጫማ በዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ የዮ​ር​ዳ​ኖስ ውኃ ይደ​ር​ቃል፤ ከላይ የሚ​ወ​ር​ደ​ውም ውኃ ይቆ​ማል።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች