Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:4 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ለይ​ስ​ሐ​ቅም ያዕ​ቆ​ብ​ንና ዔሳ​ውን ሰጠ​ሁት፤ ለዔ​ሳ​ውም የሴ​ይ​ርን ተራራ ርስት አድ​ርጌ ሰጠ​ሁት፤ የያ​ዕ​ቆ​ብም ልጆች ወደ ግብፅ ወረዱ፤ በዚ​ያም ታላቅ ሕዝብ ሆኑ፤ በዙም፤ በረ​ቱም፤ ግብ​ፃ​ው​ያ​ንም መከራ አጸ​ኑ​ባ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ለይሥሐቅ ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም ኰረብታማውን የሴይርን ምድር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብና ልጆቹ ግን ወደ ግብጽ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብጽ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁ፤ ለዔሳውም የኤዶምን ኮረብታማ አገር ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ነገር ግን ያዕቆብና ልጆቹ ወደ ግብጽ ወረዱ፤

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፥ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፥ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብፅ ወረዱ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:4
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ያዕ​ቆ​ብም ወደ ወን​ድሙ ወደ ዔሳው ወደ ሴይር ምድር ወደ ኤዶም ሀገር በፊቱ መል​እ​ክ​ተ​ኞ​ችን ላከ፤


ዔሳ​ውም በሴ​ይር ተራራ ተቀ​መጠ፤ ዔሳ​ውም ኤዶም ነው።


በሴ​ይር ተራራ የሚ​ኖሩ የኤ​ዶ​ማ​ው​ያን አባት የዔ​ሳው ትው​ል​ድም እን​ዲህ ነው።


እን​ዳ​ያ​ጠ​ፋ​ቸው የቍ​ጣ​ውን መቅ​ሠ​ፍት ይመ​ልስ ዘንድ የተ​መ​ረ​ጠው ሙሴ በመ​ቅ​ሠ​ፍት ጊዜ በፊቱ ባይ​ቆም ኖሮ፥ ባጠ​ፋ​ቸው ነበር አለ።


ሚስ​ትህ በቤ​ትህ እል​ፍኝ ውስጥ እን​ደ​ሚ​ያ​ፈራ ወይን ትሆ​ና​ለች፤ ልጆ​ች​ህም በማ​ዕ​ድህ ዙሪያ እንደ አዲስ የወ​ይራ ተክል ይሆ​ናሉ።


“ያዕ​ቆ​ብም ወደ ግብፅ ወረደ፥ እር​ሱም አባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ሞቱ።


የሴ​ይ​ርን ተራራ ለዔ​ሳው ልጆች ርስት አድ​ርጌ ስለ ሰጠሁ እኔ ከም​ድ​ራ​ቸው የጫማ መር​ገጫ ታህል እን​ኳን አል​ሰ​ጣ​ች​ሁ​ምና አት​ጣ​ሉ​አ​ቸው።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች