Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ

- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:23 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እር​ሱም፥ “አሁን እን​ግ​ዲህ በእ​ና​ንተ ዘንድ ያሉ​ትን ሌሎች አማ​ል​ክት አርቁ፤ ልባ​ች​ሁ​ንም ወደ እስ​ራ​ኤል አም​ላክ ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አቅኑ” አላ​ቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ኢያሱም፣ “እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር መልሱ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እርሱም እንዲህ አላቸው፦ “አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶች አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ ጌታ አዘንብሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 እርሱም “እንግዲያውስ በመካከላችሁ የሚገኙትን ባዕዳን አማልክት አስወግዱ፤ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አድርጉ” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እርሱም፦ አሁን እንግዲህ በመካከላችሁ ያሉትን እንግዶች አማልክት አርቁ፥ ልባችሁንም ወደ እስራኤል አምላክ ወደ እግዚአብሔር አዘንብሉ አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:23
16 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

“አሁ​ንም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ፍሩት፤ በእ​ው​ነ​ትና በቅ​ን​ነ​ትም አም​ል​ኩት፤ አባ​ቶ​ቻ​ች​ሁም በወ​ንዝ ማዶ፥ በግ​ብ​ፅም ውስጥ ያመ​ለ​ኩ​አ​ቸ​ውን ሌሎች አማ​ል​ክት ከእ​ና​ንተ አርቁ፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አም​ልኩ።


ጆሮህ ጥበብን ትሰማለች፥ ልብህንም ወደ ማስተዋል ታዘነብላለህ። ልብህንም ልጅህን ለመምከር ታቀርባለህ፥


ወደ ቀኝም ተመ​ልሼ አየሁ፥ የሚ​ያ​ው​ቀ​ኝም አጣሁ፤ መሸ​ሸ​ጊ​ያም የለ​ኝም፥ ስለ ሰው​ነ​ቴም የሚ​መ​ራ​መር የለም።


የብር አማ​ል​ክ​ትን አታ​ም​ልኩ፤ የወ​ርቅ አማ​ል​ክ​ት​ንም አታ​ም​ልኩ። የዕ​ን​ጨ​ትና የድ​ን​ጋይ አም​ላ​ክ​ንም አታ​ም​ልኩ፤ እን​ዲህ ያለ አም​ላ​ክን ለእ​ና​ንተ አታ​ድ​ርጉ።


ተመ​ል​ሰ​ውም ከጥ​ላው ሥር ይቀ​መ​ጣሉ፤ በሕ​ይ​ወ​ትም ይኖ​ራሉ፤ ከእ​ህ​ሉም የተ​ነሣ ይጠ​ግ​ባሉ፤ እንደ ወይ​ንም አረግ ያብ​ባሉ ፤ መታ​ሰ​ቢ​ያ​ውም እንደ ሊባ​ኖስ ወይን ይሆ​ናል።


በመ​ን​ገ​ዱም ሁሉ እን​ሄድ ዘንድ፥ ለአ​ባ​ቶ​ቻ​ች​ንም ያዘ​ዛ​ትን ትእ​ዛ​ዙ​ንና ሥር​ዐ​ቱን እን​ጠ​ብቅ ዘንድ፥ ልባ​ች​ንን ወደ እርሱ ይመ​ልስ።


አም​ላ​ካ​ችን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከአ​ባ​ቶ​ቻ​ችን ጋር እንደ ነበረ ከእ​ኛም ጋር ይሁን፤ አይ​ተ​ወን፤ አይ​ጣ​ለ​ንም፤


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች