Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 24:21 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 ሕዝ​ቡም ኢያ​ሱን፥ “እን​ዲህ አይ​ሁን፤ ነገር ግን እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እና​መ​ል​ካ​ለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 ሕዝቡ ግን ኢያሱን፣ “የለም! እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 ሕዝቡም ኢያሱን፦ “እንዲህ አይሁን፤ ነገር ግን ጌታን እናገለግላለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 ሕዝቡም ለኢያሱ “ይህ ከቶ አይደረግም! እኛ እግዚአብሔርን እናመልካለን” አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 ሕዝቡም ኢያሱን፦ እንዲህ አይሁን፥ ነገር ግን እግዚአብሔርን እናመልካለን አሉት።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 24:21
9 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

ሕዝ​ቡም ሁሉ አንድ ቃል ሆነው፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ፤ ሙሴም የሕ​ዝ​ቡን ቃል ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አደ​ረሰ።


ሙሴ​ንም፥ “አንተ ከእኛ ጋር ተና​ገር፤ ነገር ግን እን​ዳ​ን​ሞት እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ከእኛ ጋር አይ​ና​ገር” አሉት።


ሙሴም ገባ፤ ለሕ​ዝ​ቡም የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ቃሎች ሁሉ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንም ሁሉ ነገረ፤ ሕዝ​ቡም ሁሉ በአ​ንድ ድምፅ፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የተ​ና​ገ​ራ​ቸ​ውን ቃሎች ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” ብለው መለሱ።


የቃል ኪዳ​ኑ​ንም መጽ​ሐፍ ወስዶ ለሕ​ዝቡ አነ​በ​በ​ላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያለ​ውን ሁሉ እን​ሰ​ማ​ለን፤ እና​ደ​ር​ጋ​ለ​ንም” አሉ።


ይህ፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ይላል፤ ያም በያ​ዕ​ቆብ ስም ይጠ​ራል፤ ይህም፦ እኔ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ነኝ ብሎ በእጁ ይጽ​ፋል፤ በእ​ስ​ራ​ኤ​ልም ስም ይጠ​ራል።”


አን​ተም በመ​ን​ገዱ ትሄድ ዘንድ፥ ሥር​ዐ​ቱ​ንና ትእ​ዛ​ዙን፥ ፍር​ዱ​ንም ትጠ​ብቅ ዘንድ፥ ቃሉ​ንም ትሰማ ዘንድ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እርሱ አም​ላ​ክህ እን​ዲ​ሆን ዛሬ መር​ጠ​ሃል።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ትታ​ችሁ ሌሎ​ችን አማ​ል​ክት ብታ​መ​ልኩ፥ መል​ካ​ምን ባደ​ረ​ገ​ላ​ችሁ ፋንታ ተመ​ልሶ ክፉ ነገር ያደ​ር​ግ​ባ​ች​ኋል፤ ያጠ​ፋ​ች​ሁ​ማል” አላ​ቸው።


ኢያ​ሱም ሕዝ​ቡን፥ “እን​ድ​ታ​መ​ል​ኩት እና​ንተ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን እንደ መረ​ጣ​ችሁ በራ​ሳ​ችሁ ላይ ምስ​ክ​ሮች ናችሁ” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ምስ​ክ​ሮች ነን” አሉ።


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች