Biblia Todo Logo
የመስመር ላይ መጽሐፍ ቅዱስ
- ማስታወቂያዎች -




ኢያሱ 22:8 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 “በብዙ ብል​ጥ​ግና፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ከብት፥ በብ​ርም፥ በወ​ር​ቅም፥ በና​ስም፥ በብ​ረ​ትም፥ በእ​ጅ​ግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታ​ችሁ ተመ​ለሱ፤ የጠ​ላ​ቶ​ቻ​ች​ሁ​ንም ምርኮ ከወ​ን​ድ​ሞ​ቻ​ችሁ ጋር ተካ​ፈሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንዲህም አላቸው፤ “ብዙ ሀብት ይዛችሁ ማለትም አያሌ የከብት መንጋ፣ ብርና ወርቅ፣ ናስና ብረት እንዲሁም ቍጥሩ እጅግ የበዛ ልብስ ይዛችሁ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ ከጠላት የተገኘውንም ይህን ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋራ ተካፈሉት” አላቸው።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 እንዲህም አላቸው፦ “በብዙ ሀብት እጅግም ብዙ በሆነ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ እጅግም ብዙ በሆነ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፤ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲህም አላቸው፤ “እነሆ፥ አሁን በምርኮ ያገኛችሁትን ብዙ ከብት፥ ብር፥ ወርቅ፥ ነሐስ፥ ብረትና ብዙ ልብሶች ይዛችሁ ወደ መኖሪያችሁ ልትመልሱ ስለ ሆነ ከጠላቶቻችሁ በምርኮ ያገኛችሁትን ምርኮ ከዘመዶቻችሁ ጋር ተካፈሉ።”

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 በብዙ ብልጥግና በእጅግም ብዙ ከብት፥ በብርም፥ በወርቅም፥ በናስም፥ በብረትም፥ በእጅግም ብዙ ልብስ ወደ ቤታችሁ ተመለሱ፥ የጠላቶቻችሁንም ምርኮ ከወንድሞቻችሁ ጋር ተካፈሉ።

ምዕራፉን ተመልከት ቅዳ




ኢያሱ 22:8
12 ተሻማሚ ማመሳሰሪያዎች  

በገ​ለ​ዓድ ምድር እን​ስ​ሶ​ቻ​ቸው በዝ​ተው ነበ​ርና በም​ሥ​ራቅ በኩል ከኤ​ፍ​ራ​ጥስ ወንዝ ጀምሮ እስከ ምድረ በዳው መግ​ቢያ ድረስ ተቀ​መጠ።


እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም መን​ግ​ሥ​ቱን በእጁ አጸና፤ ይሁ​ዳም ሁሉ እጅ መንሻ ለኢ​ዮ​ሳ​ፍጥ አመጣ፤ እጅ​ግም ብዙ ብል​ጥ​ግ​ናና ክብር ሆነ​ለት።


ለሕ​ዝ​ቅ​ያ​ስም እጅግ ብዙ ሀብ​ትና ክብር ነበ​ረው፤ ለብ​ርና ለወ​ር​ቅም፥ ለከ​በ​ረው ዕን​ቍና ለሽ​ቱው፥ ለጋ​ሻ​ውና ውድ ለሆ​ነው ዕቃ ሁሉ ግምጃ ቤቶ​ችን ሠራ።


በደጅ የሚ​ቀ​መጡ በእኔ ይጫ​ወ​ታሉ፤ ወይን የሚ​ጠ​ጡም በእኔ ይዘ​ፍ​ናሉ።


ረጅም ዕድሜና የሕይወት ዘመን በቀኝዋ ነው። ባለጠግነትና ክብርም በግራዋ፥ ከአፏ ጽድቅ ይወጣል። ሕግንና ምጽዋትንም በአንደበትWa ትለብሳለች።


ምር​ኮ​ው​ንም በተ​ዋ​ጉ​ትና ወደ ሰልፍ በወ​ጡት፥ በማ​ኅ​በ​ሩም ሁሉ መካ​ከል ትከ​ፍ​ላ​ላ​ችሁ።


አሁ​ንም የተ​ወ​ደ​ዳ​ችሁ ወን​ድ​ሞ​ቻ​ችን ሆይ፥ የጸ​ና​ች​ሁና የማ​ት​ና​ወጡ ሁኑ፤ ዘወ​ትር በጎ ምግ​ባ​ርን አብ​ዝ​ታ​ችሁ ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አበ​ር​ክቱ፤ ስለ ጌታ​ችን መድ​ከ​ማ​ችሁ ለከ​ንቱ እን​ዳ​ይ​ደለ ታው​ቃ​ላ​ች​ሁና።


የክ​ር​ስ​ቶስ የመ​ስ​ቀሉ ተግ​ዳ​ሮት ከግ​ብፅ ሀብት ሁሉ ይልቅ እጅግ የሚ​በ​ልጥ ባለ​ጠ​ግ​ነት እን​ደ​ሚ​ሆን ዐው​ቆ​አ​ልና፥ ዋጋ​ው​ንም ተመ​ል​ክ​ቶ​አ​ልና።


ወደ እዚ​ያም ባደ​ረ​ሰው ጊዜ፥ እነሆ፥ ከፍ​ል​ስ​ጥ​ኤ​ማ​ው​ያ​ንና ከይ​ሁዳ ምድር ከወ​ሰ​ዱት ከብዙ ምርኮ ሁሉ የተ​ነሣ በል​ተው፥ ጠጥ​ተው፥ የበ​ዓ​ልም ቀን አድ​ር​ገው፥ በም​ድር ሁሉ ላይ ተበ​ት​ነው አገ​ኛ​ቸው።


ይህ​ንስ ነገር ማን ይሰ​ማ​ች​ኋል? እና​ንተ ከእ​ነ​ርሱ አት​በ​ል​ጡ​ምና ወደ ጦር​ነት በሄ​ዱት ድርሻ ልክ ጓዝ የጠ​በቁ ሰዎች ድርሻ እን​ዲሁ ነው።”


ተከተሉን:

ማስታወቂያዎች


ማስታወቂያዎች